1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በመላ ኢትዮጵያ ድንገተኛ የኤሌክትሪክ መቋረጥ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 15 2013

በመላዉ ኢትዮጵያ ዛሬ ቀትር ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር የሐገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ባለስልጣን ዐስታወቀ። በድንገት የተቋረጠው ኤሌክትሪክ በአንዳንድ አካባቢዎች ከሦስት ሰአታት ግድም በኋላ መመለሱም ተገልጧል።

Äthiopien | Elektrizitätswerkswerke Addis Abeba
ምስል፦ DW/S. Muche

ኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠው በድንገት ነበር

This browser does not support the audio element.

በመላዉ ኢትዮጵያ ዛሬ ቀትር ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር የሐገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ባለስልጣን ዐስታወቀ። በድንገት የተቋረጠው ኤሌክትሪክ በአንዳንድ አካባቢዎች ከሦስት ሰአታት ግድም በኋላ መመለሱም ተገልጧል። የመስሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳሬክተር ሞገስ መኮንን ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት ዛሬ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ግድም ዋና ከተማ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ሐገሪቱ ኤሌክትሪክ ተቋርጧል። አቶ ሞገስ አክለዉ እንዳሉት መስሪያ ቤታቸዉ ከሶስት ሰዓት ጥረት በኋላ ከቀኑ 10 ሰዓት ግድም ጀምሮ በአዲስ በአበባ አንዳንድ አካባቢዎችና በሌሎች የተወሰኑ ከተሞችም የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ እንዲመለስ አድርጓል። ቃለመጠይቊ ከተደረገ በኋላ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መመለሱም ተገልጧል። ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ፦ «ደረጃ በደረጃ የተቀሩትን አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ የማድረግ ሥራም በመከናወን ላይ» እንደሚገኝ  በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሩ ላይ ይፋ አድርጓል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW