1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመቀሌ ለቀናት ሲካሄድ የቆየው የተፈናቃዮች ተቃውሞ ዛሬ ተጠቀቀ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሐሙስ፣ ጥር 8 2017

በመቐለ ለቀናት ሲካሄድ የነበረው የተፈናቃዮች የተቃውሞ ሰልፍ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።ሰልፈኞቹ የክልሉ አስተዳደር አካላት ተፈናቃዮችን ወደቦታቸው እንዲመልሱ፥ የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ፤ለክልሉ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ እና ለህወሓት መሪ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጥያቄአቸውን በደብዳቤ አቅርበዋል።

ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸውን  በደብዳቤ አቅርበዋል።
ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸውን ለክልሉ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ እና ለህወሓት መሪ ዶ/ር ደብረፂዮን በደብዳቤ አቅርበዋል።ምስል Million Hailesilassie/DW

በመቀሌ ለቀናት ሲካሄድ የቆየው የተፈናቃዮች ተቃውሞ ዛሬ ተጠቀቀ

This browser does not support the audio element.

ለቀናት በመቐለ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ የሰነበቱ ሰልፈኞች የክልሉ አስተዳደር አካላት ተፈናቃዩ ወደቦታው እንዲመልሱ፥ የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ ጠየቁ። ሰልፈኞቹ ለፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ እና ለህወሓት መሪ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጥያቄአቸው በደብዳቤ አቅርበዋል።

ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ተለከታታይ ቀናት ያለማቋረጥ በመቐለ ሲደረግ የሰነበተው ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ ሰልፍ ዛሬ ንጋት ላይ ተገባዷል። ተፈናቃዮቹ ከሶስት ቀናት እና ለሊት የአደባባይ ቆይታቸው በዋነኝነት መንግስት ወደ ቀዬአቸው እንዲመልሳቸው የጠየቁ ሲሆን፥ አራት ዓመት በዘለቀ የመጠልያ ኑሮአቸው እየደረሰባቸው ያለ የከፋ ችግርም ዓለም ይወቀው ብለዋል። ማእከሉ መቐለ ሮማናት አደባባይ አድርጎ ሲካሄድ በሰነበተው የተቃውሞ ሰልፍ ከተፈናቃዮቹ በተጨማሪ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች በስፋት የተሳተፉበት ሲሆን በይፋዊ የሰልፉ መዝግያ ደግሞ የክልሉ አስተዳደር ባለስልጣናት ተፈናቃዮቹ እንዲመልሱ፥ የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ከስልጣናቸው ሊወርዱ ይገባል ተብሎ ተገልጿል።

ሰልፈኞቹ የክልሉ አስተዳደር አካላት ተፈናቃዮችን ወደቦታቸው እንዲመልሱ፥ የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጠይቀዋል።ምስል Million Hailesilassie/DW

ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ዳንኤል ነጋሽ "የተፈናቃዮች ጉዳይ ከጠባብ የፖለቲካ አጀንዳ በላይ መሆኑ አምናችሁ፥ ሌላ የፖለቲካ ቁሩቁሳችሁ አቆይታችሁ በጋራ ጉዳይ ትኩረት አድርጋችሁ ወደ ቀዬአችን እንድትመልሱን ጥሪ እያቀረብን፥ ይህ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ ትግራይ ከዚህ የሚበልጥ አጀንዳ ስለሌላት ሐላፊነታችሁ በአስቸኳይ ለሚችል አሳልፋችሁ እንድትሰጡ ጥሪ እናቀርባለን" ብለዋል።

ተፈናቃዮቹ በትላንትናው ዕለት ለትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት፣ ለህወሓት ሊቀመንበር እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የሰልፈኛው ጥያቄ በፅሑፍ ቀርቧል። የሰልፉ አስተባባሪ የሆነው ፅላል ሲቪል ማሕበረሰብ ትግራይ ትላንት ባሰራጨው መግለጫው ደግሞ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት የገባው ግዴታ እንዳያከብር የጠየቀ ሲሆን ተፈናቃዮች የመመለስ መንግስታዊ ሐላፊነቱም ይመልስ ብሏል።

ሙሉ ዘገባውን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ
ፀሐይ ጫኔ

 

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW