1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በመተከል ዞን ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደሰላም መመለሳቸው

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 26 2015

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ 90 የሚደርሱ ታጣቂ አባላት በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ትጥቃቸውን ለመንግሥት ማስረከባቸው ተገለጸ።

Äthiopien | Assosa
ምስል፦ Negassa Desalegn /DW

ታጣቂዎች ወደሰላም ተመለሱ

This browser does not support the audio element.

የተመከል ዞን ለረጅም ጊዜ በጊዜያ አስተዳደር /ኮማንድ ፖስት/ ሲተዳደር የቆየ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዞኑ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪን በመቀበል ትጥቅ እየፈቱ ይገኛሉ። በዞኑ በታጣቂዎች እንቅስቃሴ እና የተለያዩ ጥቃቶች ምክንያት በዞኑ ብቻ ከ2 መቶ 60 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው ቆይተዋል። በትናንትው ዕለትም በዞኑ ዳንጉር እና ጉባ ወረዳዎች ይንቀሳቀሱ የነበሩ  ታጣቂዎች የተደረገላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ተመልሰዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽ ኮሚሽነር ሐሩን ኡመር ማክሰኞ ዕለት ማምሻን 72 የሚደርሱት የታጠቁ እና ሌሎች ድጋፍ ሲያደርጉላቸው የነበሩ ባጠቃላይ  90 የታጣቂ ቡድኑ አባላት ትጥቃቸውን ለመንግሥት ማስረከባቸውን አስታውቀዋል።  በዞኑ በእጀባ ይሰጥ የነበረው የመጓጓዣ አገልግሎት በአሁን ጊዜ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተከፍተው አገልግሎቱ ወደ  መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሱንም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። በዞኑ ሰላም በመስፈኑ ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ የነበሩ የተፈናቀሉ ዜጎችም ወደ የቀድሞ ቀያቸው መመለሳቸውን እና 24ሺህ የሚደርሱት ብቻ በመጠለያ እንደሚገኙም ተገልጸዋል፡፡

የጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ ከክልሉ መንግሥት ጋር ስምምነት ከተደረገ ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ወዲህ በድርጅቱ ስም ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችት ትጥቃቸውን ፈተው ወደ ኅብረተሰቡ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል። የተመለሱት ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም ጥሪ ተደርጎላቸው እንደነበር ጠቁሟል። የሰላም ጥሪን የማይቀበሉ ታጣቂዎች ድርጅቱን የማይወክን ኃላፊነትም እንደማይስዱ ተናግረዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሲንቀሳቁ ከነበሩ ሁለት ታጣቂ ቡድን የቤ.ኔ.ን እና ጉህዴን የጠባሉ ቡድን ጋር የክልሉ መንግስት በተለያዩ ወቅት ስላምም ስምምነት ላይ ከደረሰ ወዲህ በክልሉ ሁሉም ስፍራዎች ሰላም መስፈኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል። ለሁለት ዓመታት ተዘግቶ የቆና በእጀባ ብቻ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው  አሶሳን ከመተከል ጋር የሚያገናኝ መንገድም በአሁኑ ወቅት ያለ እጀባ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። በክልሉ ባጠቃላይ በነበረው የጸጥታ ችግር የወደሙ ተቋማትና መኖርያ ቤቶች መልሶ ለማቋቋም በቢሊዮን የሚገመት ገንዘብ እንደሚያስፈልገው  ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ላይ በተደረገው ጥናት ማረጋገጡን የክልሉ መንግሥት ይፋ አድርጓል።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW