1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመተከል ዞን የተቀሰቀሰ ግጭት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 6 2013

ሁለት ሚኒባሶች መቃጠላቸውንና በሚኒባሱ የነበሩ ሰዎች ላይም ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።ዶቼቬለ የጉዳቱን መጠን ከአካባቢው ኮማንድ ፖስት በስልክ ለማረጋገጥ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።የመተከል ዞን «በግልገል በለስ ከተማና ቀጠናው ለጥፋት እና ለብጥብጥ ተሰማርተው የሚገኙ አካላትን ሁሉም በየአካባቢው በመቀናጀት መመከት አለበት» ሲል አሳስቧል

Karte Äthiopien Metekel EN

በመተከል ዞን የተቀሰቀሰ ግጭትና የደረሰ ጥቃት

This browser does not support the audio element.

 
በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ውስጥ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ተጀመረ በተባለው አለመግባባት በተቀሰቀሰ ግጭት ምክንያት የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ሁለት ሚኒባሶች በታጣቂዎች በዕለቱ መቃጠላቸውን እና በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ላይም ጉዳት መድረሰን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ዶቼቬለ የጉዳቱን መጠን ከአካባቢው ኮማንድ ፖስት በስልክ ለማረጋገጥ ያደረገው ጥረት ስልክ ባለማንሳታቸው አልተሳካም። መተከል ዞን የኮሙኒኬሽን መምሪያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ«በግልገል በለስ ከተማና ቀጠናው ለጥፋት እና ለብጥብጥ ተሰማርተው የሚገኙ አካላትን ሁሉም በየአካባቢው በመቀናጀት መመከት አለበት» ሲል  አሳስቧል። በከተማዋ እና አካባቢዋ የጠላት አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ያላቸውን ኃይሎችን በመከታተል «በቁጥጥር ስር እንድታውሉ» በማለትም ጥሪ አቅርቧል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW