1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ ላይ የቀረበ ጥሪ

ሰለሞን ሙጬ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 3 2017

ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ "ዴሞክራሲን ከማስፈንና የመገናኛ ብዙኃንን ነጻነትን ከማረጋገጥ አንፃር አስቻይ የሕግ ማዕቀፎችን የሚንድና ወደኋላ የሚጎትት እንዳይሆን" ሲሉ 14 የሙያ ማህበራት በጋራ ጠየቁ።

Äthiopien FDRE-House
ምስል Ethiopian Press Agency

አዲሱ የመገናኛ ብዙኃን ረቂቅ ተቃዉሞ ገጠመው

This browser does not support the audio element.

በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ ላይ የቀረበ ጥሪ

 

ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ "ዴሞክራሲን ከማስፈንና የመገናኛ ብዙኃንን ነጻነትን ከማረጋገጥ አንፃር አስቻይ የሕግ ማዕቀፎችን የሚንድና ወደኋላ  የሚጎትት እንዳይሆን" ሲሉ 14 የሙያ ማህበራት በጋራ ጠየቁ።

ማሻሻያው በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የሚስተዋሉ ሕግ እና የሥነ ምግባር ጥሰቶችን ለማረምና የሕዝብ ጥቅምን ለማስጠበቅ ይረዳል የተበለን የቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋት ታስቦ መዘጋጀቱ ተገልጿል። በአዲሱ የማሻሻያ ረቂቁ የፖለቲካ ፓርቲ አባል የሆኑ ሰዎች የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የቦርድ አባል መሆን አይችሉም በሚል ተደንግጎ የነበረው አንቀጽ መውጣቱ የሙያ ማህበራቱ እጅግ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።

የሚዲያ ነፃነትና የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጥሪ

ረቂቅ የማሻሻያ አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዝርዝር በመታየት ላይ ይገኛል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም  አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የመራው ሲሆን፣ 14ት የሙያ ማህበራት እና ሲቪክ ድርጅቶች  ይህ ጉዳይ ያሳስበናል በሚል የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

 

"የአዋጁ ማሻሻያ አስፈላጊነት ላይ ገለልተኛ ጥናት ባልተደረገበት፣ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይት ባልተካሔደበት ሁኔታ ረቂቁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡ በእጅጉ" አሳስቦናል ሲሉም አቤት ብለዋል።"ማሻሻያውን ለማዘጋጀት የተሔደበት መንገድ ግልጽነትና አሳታፊነት የጎደለው ሲሆን፣ የረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት በገለልተኛ አካል በተሠራ ጥናት ስለመለየቱ የቀረበ ማስረጃ የለም።" ሲሉም ተቃውመዋል። መግለጫውን በጋራ ካወጡት ድርጅቶች መካከል የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሄኑትን ዶክተር ሞገስ ደምሴን ማብራሪያ ጠይቀናቸዋል።

የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ደረጃ ማሽቆልቆል

"እነዚህ ማሻሻያዎች ምናልባት የሚዲያ ምህዳሩን የማጥበብ፣ የዲሞክረሲ እና የሰብዓዊ መብት ነፃነቶችንም ችግር ላይ ሊጥሉ ይችላሉ"በሌላ በኩል የረቂቅ አዋጁ የተለያዩ አንቀፆች በሥራ ላይ የሚገኘው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ጥበቃ የሚሰጣችውን ነጻነቶች የሚገድብና የሚዲያ ተቆጣጣሪውን አካል በአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ውስጥ ይከተዋል የሚል ስጋት እንዳላቸው ድርጅቶቹ ሥጋታቸውን ጠቅሰዋል።

ለአብነትም የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የቦርዱ አባላት ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ወይም ተቀጣሪነት የሚከለከሉበትን ሁኔታ የሚደነግገው ክፍል መሰረዝ ከዋና የይዘት ለውጦች መካከል መሆኑን አንስተዋል።ምስል Solomon Muchie/DW

 

ለአብነትም የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የቦርዱ አባላት ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ወይም ተቀጣሪነት የሚከለከሉበትን ሁኔታ የሚደነግገው ክፍል መሰረዝ ከዋና የይዘት ለውጦች መካከል መሆኑን አንስተዋል።በነባሩ አዋጅ ለቦርዱ ተሰጥተው የነበሩት የፈቃድ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት አለማደስ፣ ማገድ፣ መሰረዝ፣ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት የመሳሰሉት ኃላፊነቶች አሁን ለባለሥልጣኑ መሰጠታቸው ሥልጣንን ጠቅልሎ ለአንድ አካል ከመስጠትና በሒደትም ላልተገባ ተፅዕኖ በር ከመክፈቱ በተጨማሪ "የባለሥልጣኑን ገለልተኝነትና ነፃነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ" መሆኑንም ጠቀሰዋል። ይህ ጥያቄ ረቂቁ ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅትም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተነስቶ ነበር።

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እንግልት የሚሰንደው አዲስ ድረ-ገጽ

ከሲቪክ ድርጅቶች የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች እንዲሁም ከሙያ ማህበራት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበርን ጨምሮ በጋራ መግለጫ ያወጡት 14ቱ ተቋማት የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ መንፈስ ዴሞክራሲን ከማስፈንና የመገናኛ ብዙኃንን ነጻነትን ከማረጋገጥ አንፃር የነበረውን አስቻይ ያሉትን የሕግ ማዕቀፍ የሚንድና ወደኋላ  የሚጎትት እንዳይሆን በአጽንኦት እንጠይቃለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃንን ይዞታ የቃኘው ውይይት

ካርድ ባለፈው ሳምንት ባወጣው በሲቪል ማህበረሰቡ እንዲሁም በግለሰብ ነፃነት የሚደረጉ "ስልታዊ" ያላቸው አፈናዎች በሀገሪቱ ላይ የሚደረጉ የዴሞክራሲ ጥረቶች ላይ ከፍተኛ ሥጋት" መደቀናቸውን ፤ "ከ2011 ዓ. ም ጀምሮ ከ 200 ጋዜጠኞች በላይ ታስረዋል፣ ይህም ነፃ የመገናኛ ብዙኃን እንዲዘጉ አድርጓል፣ ከ2012 ዓ.ም ወዲህ ደግሞ 54 የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች በደረሰባቸው እንግልት ምክንያት ከሀገር ለመሰደድ ስለመገደዳቸው ገልጾ ነበር።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW