1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በምያንናማር የቀሪ ታጋች ኢትዮጵያዉያን ዕጣ ፈንታ አልታወቀም

ሥዩም ጌቱ
ቅዳሜ፣ ሰኔ 21 2017

በምያንማር ከአጋቾች አምልጠው በካምፕ ውስጥ ከነበሩ 751 ኢትዮጵያውያን መካከል የሆኑት የመጨረሻዎቹ 49 ታጋቾች ከትናንትባለፈው ረቡዕ ወደ አገር መግባታቸውን የወላጆች ኮሚቴ አስተባባሪዎች ለዶይቼ ቬለ ገለጹ፡፡

Thailand Myan Scam Centers | Verschleppte Ausländer, die in Scam Centers arbeiten mussten, werden gerettet  FILE PHOTO: Trafficked scam center victims in Myanmar are sent to Thailand before repatriation, in Tak
ምስል፦ Chalinee Thirasupa/REUTERS

ሚያንማር ውስጥ ታግተው ከነበሩት ውስጥ በርካቶች ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል።

This browser does not support the audio element.

ወደ አገራቸው ተመልሰው የተጠናቀቁት ኢትዮጵያውያን ከየካቲት ወር አንስቶ ለወራት በአሰቃቂ ሁኔታ በጦርነት ቀጣና በብዙ ስጋትም ውስጥ መቆየታቸውን ይገልጻሉ። በምያንማር የተጎጂ ወጣቶች ቤተሰቦች አስተባባሪ ወ/ሮ አበበች ሲመል ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩትም፤ “ምያንማር የነበሩ ከ751 ልጆች ከሌላ የአፍሪካ አገራት ወጣቶች ጋር አምጸው የወጡት ከ “ዴሞክራቲክ ካረን ቤነቮለንት አርሚ (DKBA)” እና “ቦርደር ጋርድ ፎርስ” (BGF) በተባሉት የምያንማር አማጺያን እጅ የነበሩ ናቸው” ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከኢትዮጵያ አየርመንገድ እና ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከአጋቾች እጅ ከወጡት ከእነዚህ 751 ከትናንት በስቲያ ረቡዕ የመጨረሻ ዙር የሆነው ቀሪ 49 ዜጎች ወደ አገር ቤት መግባታቸውንም አስረድተዋል፡፡

በአጋቾች እጅ ያሉ 42 ኢትዮጵያውን እጣ ፈንታቸው አልታወቀም

ከአጋቾች ከወጡት ወደ አገር ያልተመለሰ ምንም የሚቀር ዜጋ የለም ያሉን አስተባባሪዋ አሁንም ድረስ በአጋቾች እጅ ያሉ 42 ኢትዮጵያውን ግን እጣፈንታቸው አለመታወቁንም በአስተያየታቸው አክለዋል፡፡ “ከአጋቾች እጅ መውጣት እየፈለጉ ከዚህ ቀደም ሌሎች ስወጡ አጋቾቹ ያስቀሯቸው 42 ወጣቶች አሁን ላይ በሶስት ኩባንያዎች ውስጥ በጉልበት ብዝበዛ ላይ ይገኛሉም” በማለት የእነዚህ በፖሊስ እጅ ያልገቡ ወጣቶች ህይወት በአደጋ ላይ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በታይላንድ እና በማይናማር ለመስራት የሚከፍሉት ዋጋ

በተጎጂ ወጣቶቹ እንግልት የደላሎች ሚና

ኢትዮጵያውያኑ ከሌሎች አገራት ዜጎች ጋር ወደ እነዚህ ካምፖች የገቡት ጥሩ ገንዘብ እንደሚያገኙ ተነግሯቸው ወደ ታይላንድ ከተወሰዱ በኋላ በምያንማር ለሚገኙ የወንጀል ቡድኖች በመሸጣቸው ነው የሚሉት የአንዱ ተጎጂ ወጣት እናት ደላሎቹ ሲያቀርቡላቸው የነበረው የሚያጓጓም ጥቅም ነው ይላሉ። “የዛኔ ስሄድማ የተባለው አንደኛ የንግድ ስራ ነው በሽያጭ ስራ ላይ በመሰማራት ከ150 ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር ታገኛላችሁ የሚል ነበር” በማለት ለዚህ ደግሞ ተጠያቂ መሆን ያለባቸው እራሳቸውን የደበቁ ደላሎች አሉ

ኢትዮጵያውያኑ ከሌሎች አገራት ዜጎች ጋር ወደ እነዚህ ካምፖች የገቡት ጥሩ ገንዘብ እንደሚያገኙ ተነግሯቸው ወደ ታይላንድ ከተወሰዱ በኋላ በምያንማር ለሚገኙ የወንጀል ቡድኖች በመሸጣቸው ነው የሚሉት የአንዱ ተጎጂ ወጣት እናት ደላሎቹ ሲያቀርቡላቸው የነበረው የሚያጓጓም ጥቅም ነው ይላሉ።ምስል፦ MUNIR UZ ZAMAN/AFP/Getty Images

ሌላው የኢትዮጵያውያን ስደተኞች የመከራ መንገድ ፤ ታይላንድ ባንኮክ

ነው ያሉት፡፡ ልጃቸውን በሀሰት በመደለል ወደዚያ እንዲሄድ ያደረገችው ደላላ ላይ በፍረድ ቤት የ10 ዓመት ጽኑ እስራት እና የገንዘብ መቀጮ ተከታትለው ማስፈረዳቸውን የገለጹት አስተያየት ሰጪዋ ከስዴት ተመላሽ ተጎጂዎቹ ጋር እንኳ እዛ ድረስ ከሄዱ ደላሎች ሶስቱ በፌዴራል ፖሊስ ተይዘው በምርመራ ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

አሁን አሳሳቢው ነገር በዚያ ስለቀሩ 42 በአጋቾች እጅ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ነው ያሉን የተጎጂ ወጣቶቹ ቤተሰቦች አስተባባሪ “እኛ ልጆቻችን ገቡ ብለን አልተቀመጥንም ላልተመለሱትም እየጮህን ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ዶይቼ ቬለ ስለተቀሩት ወጣቶች እጣፈንታና መንግስት እነሱንም ለማስለቀቅ አሁን ላይ ምን እየሰራ ነው ለሚለው አስተያየት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ጋር ብደውልም ጥረቱ ለዛሬ አልሰመረም፡፡ በታጣቂዎች እጅ የነበሩትን ተጎጂዎች ለማስወጣት በጃፓን ቶኪዮ እና በሕንድ ኒው ዴልሂ በሚገኙ ኤምባሲዎች እንዲሁም በአጎራባቿ አገር ታይላንድ የሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኅብረት ሲሰሩ እንደነበር ግን ከዚህ በፊት መነገሩ ይታወሳል።

ከምያንማር መውጪያ ያጡት ኢትዮጵያውያን

ተሰዳጅ ወጣቶቹ በመነሻ የመጀመሪያ ደረጃ ያላቸው እና ሁለተኛ እና ሶስተና ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ያላቸው እንዲሁም ሜዲካል ዶክተሮች እንደሚገኙበትም የተጎጂ ቤተሰብ አስተባባሪዎቹ ያስረዳሉ፡፡ ይህም በሀሰት ይከፈላል በተባለው ከፍተኛ ደመወዝ በመታለል ነው ተብሏል፡፡

በታጣቂ አጋቾች እጅ የነበሩ 751 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገር መመለስ የተጀመረው ሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም. ላይ አንደነበርም አይዘነጋም።

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW