በማድመጥ መማር ታሪክዎን ማሰማት ይፈልጋል
ዓርብ፣ ግንቦት 10 2004ውድድሩ ምንን በተመለከተ ነው?
«በማድመጥ መማር» የእርስዎን ታሪክ ማሰማት ይፈልጋል! የእርስዎ ሀሳብ በመላው አፍሪቃ በስድስት የተለያዩ ቋንቋዎች የሚሰራጨው «የበማድመጥ መማር» አዲስ ተከታታይ ድራማ እውን እንዲሆን ያስችለዋል።
እስካሁን የበርካታ ወጣት አፍሪቃውያንን ታሪኮች አሰምተናል። ለአብነት ያህል በዓለማችን ዝነኛ የእግር ኳስ ተጫዋች የመሆን ህልም ያነገበው ዮናታን ይገኝበታል። ወይንም ደግሞ የ16 ዓመት ወጣቷ ዴዚሬን ታስታውሷት ይሆን? ከእናቷ ሞት በኋላ ታናሽ ወንድሟን የመንከባከብ ሃላፊነት በሷ ላይ ወድቆ ነበር።
አሁን ተራው የእርስዎ ነው፤ እናስ ስለ ህይወት የተማርዋቸው ወሳኝ ተሞክሮዎች የትኞቹ ናቸው? አለያም በማድመጥ መማር ድራማችን በተለይ መስማት የሚፈልጉዋቸውን ርዕሰ ጉዳዮች ይንገሩን!
እባክዎ ታሪክዎን እአአ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ. ም(ወይም በኛ አቆጣጠር እስከ ሰኔ ስምንት ቀን 2004 ዓ. ም) ድረስ በኢሜል አድራሻችን amharic@dw.de ይላኩልን።
ሽልማቱ ምንድን ነው?
የመጀመሪያ ሽልማት:
የአሸናፊው ቡድን ታሪኮች ለሚቀጥለው የበማድመጥ መማር ተከታታይ ድራማችን ይመረጣሉ። ታሪካችሁ ወደ ድራማ ተቀይሮ ሀገር ውስጥ በሚከናወነው ቀረፃ በተዋናይነት እንድትሳተፉ ይደረጋል!
ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሽልማቶች:
የCD ማጫወቻ ማሸነፍ ይችላሉ። በተጨማሪም «የበማድመጥ መማር» አርማ ያለባቸው ካናቲራዎች፣ ሲዲዎች እና ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች የተካተቱበት «የበማድመጥ መማር» እሽግ ያሸንፉ!
ማን ነው በውድድሩ መሳተፍ የሚችለው?
-ዕድሜዎ ከ25 ዓመት በታች ከሆነ።
-ቢያንስ 5 አባላት ያሉት ቡድን ውስጥ የሚገኙ ከሆነ፤ ለምሳሌ፥ በቡድን የተሰባሰባችሁ ጓደኛሞች፣ በትምህርት ቤት አለያም በወጣት ክበባት ውስጥ የምትገኙ ከሆነ።
-አሁን የሚኖሩት አፍሪቃ ውስጥ ከሆነ።
ምንድን ነው ማድረግ ያለብዎት?
-ታሪክዎን በአንድ ገፅ ይፃፉ። እባክዎ ከአንድ ገፅ እንዳያሳልፉ!
-በቡድንዎ ውስጥ የሚገኙትን አባላት ሙሉ ስም እና ዕድሜ መፃፍዎን እንዳይረሱ።
-እባክዎ የቡድንዎን ፎቶ ያካቱ።
ከዚያም ታሪክዎን በኢሜል አድራሻችን amharic@dw.de ወይንም በሚከተለው የፖስታ አድራሻችን ይላኩልን፥
ለጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ
የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት ክፍል
በማድመጥ መማር
ፖ.ሣ. ቁጥር 5676
አዲስ አበባ
የውድድሩ መዝጊያ ቀን ሰኔ 15 ፣ 2004 ዓ. ም. ነው። ከቀነ ገደቡ ውጪ የሚደርሱ ማናቸውም ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
ታሪክዎን እንጠብቃለን!