በምርጫ ታዛቢዎች መረጣ ላይ የተነሱ ትችቶች እና ምላሹ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 14 2007ማስታወቂያ
በመጪዉ ግንቦት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው ሀገር አቀፋዊ ምርጫ የሚያገለግሉ የህዝብ ታዛቢዎች ባለፈው እሁድ መመረጣቸው ተሰምቷል።« የህዝብ ታዛቢዎቹ ምርጫ በገዢው ፓርቲ አባላት የተካሄደ፣ ተመራጮቹ ባለፈው ምርጫም በታዛቢነት ያገለገሉ እና ገለልተኛም አይደሉም በማለት ተቃዋሚ ፓትቲዎች ሂደቱን ተችተዋል። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የታዛቢዎቹ ምርጫው ከባለፈው በተሻለ፣ ህዝቡን ያሳተፈ መሆኑን በመግለፅ ምርጫ ቦርዱ እርማት የሚሹ ጉዳዮች ካሉ ለማረም ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።
ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሄር
ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሰ