1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በምስራቅ አማራ እየጨመረ የመጣዉ የህፃናት ጥቃት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 18 2017

በምስራቅ አማራ ህፃናት ላይ የሚደርሰዉ ፃታዊ ጥቃት ቢጨምርም ተጎጂዎች ወደ ህግ አካል እየመጡ አይደሉም የሚሉት ሳጂን ፋጡማ አሊ አሁን በአካባቢዉ ያለዉ ጦርነት ተጎጂዎችን ወደ ህክምና ማዕከላት እንዳይመጡ እንቅፋት ሁኗል ነዉ የሚሉት።

በህፃናት ላይ የሚፈፀም ፃታዊ  ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ገለፀ
በህፃናት ላይ የሚፈፀም ፃታዊ  ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ገለፀምስል Rolf Poss/IMAGO

በምስራቅ አማራ እየጨመረ የመጣዉ የህፃናት ጥቃት

This browser does not support the audio element.

በህፃናት ላይ የሚፈፀም ፃታዊ  ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ገለፀ

ማዕከሉ በምስራቅ አማራ ፃታዊ ጥቃት ለደረሰባቸዉ ሰዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በያዝነዉ አመት እድሜያቸዉ ከሦሶት አመት ጀምሮ ባሉ ህፃናት ላይ ፆታዊ ጥቃት መፈፀሙን የማዕከሉ አስተባባሪ ሲስተር መዲና ወርቅነህ ይናገራሉ።

ጥቃቱ በአብዛኛዉ የጫት ዕፅ ተጠቃሚዎች የሚበዙበት ከተሞች ላይ  ሀይቅ፣ ኮምቦልቻ፣ ባቲ እንዲሁም ከሚሴ  በዝቶ መታየቱን ነዉ 
የማዕከሉ መረጃ የሚያሳየዉ።

በምስራቅ አማራ ህፃናት ላይ የሚደርሰዉ ፃታዊ ጥቃት ቢጨምርም ተጎጂዎች ወደ ህግ አካል እየመጡ አይደሉም የሚሉት ሳጂን ፋጡማ አሊ አሁን በአካባቢዉ ያለዉ ጦርነት ተጎጂዎችን ወደ ህክምና ማዕከላት እንዳይመጡ እንቅፋት ሁኗል ነዉ የሚሉት።

ፃታዊ ጥቃት የሚፈፅሙ ወንጀለኞች ላይየሚወሰድ ቅጣት ከዋስትና መብት ጋር ተያይዞ በተገቢዉ መንገድ ተፈፃሚ እየሆነ አይደለም የሚሉት አቃቤ ህግ ወይዘሮ አደፋሽ አባተ በርካታ ወንጀለኞች ከዋስትና ጋር በተያያዘ ጥፋት ሰርተዉ ይሰወራሉ ብለዋል።

የህግ አተረጓጎም ልዩነት መኖርና ህጉ በራሱ ያለበት  የአፈፃፀም ክፍተት አጥፊዎች ተገቢዉን ቅጣት እንዳያገኙ ምክንያት ነዉ የሚሉት በወሎ ዮንቨርስቲ የህግ ትምህርት ቤት መምህርና ጠበቃ አቶ አለሙ ዳኘዉ  አሁን እየተሻሻለ የሚገኘዉ የወንጀል ስነስርዓት ህግ ሲፀድቅ የተፈጠረዉን የህግ ክፍተት ይሞላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ኢሳያስ ገላው
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW