1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በምዕራብ አፍሪቃና በሳህል ሀገራት የተከታተሉት መፈንቅለ መንግስቶች አንድምታ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 25 2015

ከአውሮጳና በተለይም ከፈረንሳይ ጋር የቀረበ የኢኮኖሚና ወታደራዊ ትሥሥር ያላቸው የምዕራብ አፍርካና ሳህል አገሮች፤ በዚህ ፍጥነትና ብዛት በመፈንቅለ መንግስት መናጣቸው አውሮጳን አስደንግጧል፤ አሳስቧልም። የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ሚስተር ጆሴፕ ቦርየል «አስቸጋሪ ሁኔታ ነው። ይህ ሁሉ ለአውሮጳ ትልቅ የቤት ስራ ነው » ብለዋል።

Gabun | Militärputsch
ምስል AA/picture alliance

በምዕራብ አፍሪቃና በሳህል ሀገራት የተከታተሉት መፈንቅለ መንግስቶች አንድምታ

This browser does not support the audio element.

አፍሪቃ በተለይ ካአንድ አመት ተኩል ወዲህ ቀደም ሲል ከሁለት አስርት አመታት በፊት እንደነበረው በመፈንቅለ መንግስት ይናጥ ይዟል። በጊኒ፤ ማሊና ቡርኪና ፋሶ የተካሂደትን መፈንቅለ መንግስቶች ተከትሎ ካንድ ወር በፊት እንደዚሁ በኒጀር የተካሂደው መፈንቅለ መንግስት ከላይ ከታች እያራወጠ ባለበት ወቅት፤ ትናንት ማለዳ ደግሞ የጋቦን ወታደሮች በአገሪቱ ቴሌቪዥን ብቅ ብለው፤ ከሁለት ቀናት  በፊት ተመረጡ የተባሉትንና 41 አመት በስልጣን ቆይተው ያረፉትን አባታቸውን ተክተው 14 አመት አገሪቱን የመሩትን አሊ ቦንጎን ከስልጣን ማውረዳቸውን አስታወቁ ። “ በስልጣን ላይ ያለው ሀላፊነት የማይሰማው መንግስት በመሆኑና አገሪቱም ቁልቁል እይሂደችና የመፍረስ አደጋም ሊያጥማት የሚችል በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ  እኛ የሽግግር ኮሚቴ አባላት ይህን መንግስት ከስልጣን አውርደናል። ባለፈው ቅዳሜ የተደረገው ምርጫና ውጤቱም ውድቅ ሁኗል፤  በማለት ለግማሺ ምእተ አመት የቆየው የቦንጎ ስርወ መንግስት ማክተሙን አስታውቀዋል። መፈንቅለ መንግስቱ ከምርጫ ማግስት መሆኑ አግራሞትን ፈጥሯል። ሆኖም ግን የትንሿንና የነዳጅ ዘይት ባለቤትም የሆነችውን ጋቦንን ታሪክና ፖለቲካ በቅርብ ለሚከታተሉ ሁኔታው ብዙም አላስደነቃቸውም። የአፍሪካ ሪስክ ኮንስልታንሲ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ዳይሬተሯ ወይዘሮ  ቶራ ኦኮኖር እንደሚሉት የተካሂደው ምርጫና ውጤቱ ይህን የመሰለ ክስተት ማስክተሉ የሚጠበቅ ነበር ባይባልም የሚያስገርም ግን አይደለም፤ “ ሁኔታው የአንድ ቤተሰብ ማለት የቦንጎ ቤተሰብ ስርወ መንግስት የቀጠለበት ነው የሚመስለው። አሁን አሸናፊ የተባሉት አሊ ቦንጎ ክ14 አመት በፊት ነው ስልጣን ከአባታቸው የወሰዱት፤ በማለት ይህ ቅሬታ ፈጥሮ  እንደቆየና  በጎረቤት አገሮች፤ ቡርኪና ፋ፤ ማሊና ኒጀር የተካሄዱት መፈንቅለ መንግስቶችም የራሳቸውን አስተዋጾ አሳድረው ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋልየኒዠር መፈንቅለ መንግስትና ማስጠንቀቂያዉ

ከፍተኛ መኮንኖቹ “ በስልጣን ላይ ያለው ሀላፊነት የማይሰማው መንግስት በመሆኑና አገሪቱም ቁልቁል እይሂደችና የመፍረስ አደጋም ሊያጥማት የሚችል በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ  እኛ የሽግግር ኮሚቴ አባላት ይህን መንግስት ከስልጣን አውርደናል።ምስል Handout/Gabon 24/AFP

በሌላ በኩል የኒዠሩን ፕሬዝዳንት ባዙምን ወደ ስልጣን ለማምጣትና ህገመንግስታዊ ስራቱን ለመመለስ የአውሮፓ ህብረት፤ አሜሪካና የምራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማሃበረስብ ኢኩዋስ የወሰዷቸው የማዕቀብ ውሳኔዎችና ወታደራዊ ዛቻዎች ይልቁንም ለወታደርዊ ሁንታው ድጋፍ ያስገኙ ነው የሆኑት። በሊቢያ የተፈጠረውን በማስታወስ ጭምር በጎረቢቷ ኒጀር ማንኛውንም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ስትቃወም የየቆየችው አልጀሪያ ግን ከትናንት ወዲያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አህመድ አታፍ አማካይነት አዲስ የቀውስ መውጫ ዕቅድ ይፋ አድርጋለች። የኢኩዋስ አገሮችንም አማክረዋል የሚባሉት ሚስተር አታፍ በጋዜጣዊ መገለጫቸው ያቀረቡት የሰላም ሀሳብ፤ የኒዠር ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበትና  በስምምነት የሚመረጥ መሪም የተሰየመበት ለስድስት ወር የሚቆይና ህገመንግስታዊ ስራቱን ለመመለስ የሚያስችል ሁኒታ የሚፈጥር የሽግግር መንግስት እንዲመስረት የሚጠይቅ  መሆኑን ገልጸዋል። ይህ የአልጀሪያ ሀሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ ባይታወቅም ተስፋ እንዳለው ግን ይነገራል ። ካቢር አዳሙ የተባሉ የሳህል አካባቢ ተመራማሪ እንደሚሉትም ዕቅዱ ለኢኩዋስም እፎይታ የሚያስገኝ ነው፤  “ ከኢኮዋስ በኩል ችግሩን በሰላማዊ ዘዴ ለመፍታት የሚያስችል ትልቅ እድል ነው። ከጁላይ 26 ጀምሮ ኢኰስስ ህገ መንግስታዊ ስራቱን ለመመለስ ያደረጋቸው ጥረቶች አልተሳኩም፤  ይህም ኢኮዋስን ደካማ አድርጎት ቆይቷል” በማለት ይህ የአሁኑ ያልጀሪያ ሀስብ ሁንታው ካቀረበው የሶስት አመት ጊዜ የሚያንስ በመሆኑም ኢኩዋስ ሀሳቡን ሊገዛው የሚችል መሆኑን ጠቁመዋል ። በኒጀር ወታደራዊ መሪዎች በኩልም የቀረበው የሶስት አመት ግዜ ለደርድር የሚቀርብ እንደሚሆን ታዛቢዎች ይገልጻሉ። በመሆኑም በኒጀር ጉዳይ ያለው ፍጥጫ ለግዜው በዚህ ያልጀሪያ የሰላም እቅድ እልባት ሊያገኝ ይችላል የሚል ተስፋ አሳድሯል።ከመፈንቅለ መንግሥት የተረፉት አሊ ቦንጎ ማን ናቸው?

ካቢር አዳሙ የተባሉ የሳህል አካባቢ ተመራማሪ እንደሚሉትም ዕቅዱ ለኢኩዋስም እፎይታ የሚያስገኝ ነው፤  “ ከኢኮዋስ በኩል ችግሩን በሰላማዊ ዘዴ ለመፍታት የሚያስችል ትልቅ እድል ነው። ምስል Gerauds Wilfried Obangome/REUTERS

የጋቦኑን ጉዳይ  የአውሮጳ ህብረትና አሜሪካ እንደተለመደው ድርጊቱን አውግዘው ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ ወደ ስልጣናቸው እንዲመለሱ ከመጠይቁ ውጭ ለጊዜው የተባለ ነገር የለም። እሳቸው ግን በቁጥጥር ስር ካሉበት ሆነው በማህበራዊ ሜዲያ ባስተላለፉት መልክት፤ ወዳጆቻቸው ሁሉ እንዲደርሱላቸውና ካሉበት ሁኒታ እንዲያወጧቸው መጠየቃቸው ተሰምቱል።

ከአውሮፓና በተለይም ከፈረንሳይ ጋር የቀረበ የኢኮኖሚና ወታደራዊ  ትሥሥር ያላቸው የምራብ አፍርካና ሳህል አገሮች፤ በዚህ ፍጥነትና ብዛት በመፈንቅለ መንግስት መናጣቸው አውሮፓን አስደንግጧል፤ አሳስቧልም። የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ሚስተር ቦርየል ለስብሰባ ከሚገኙበት ስፔን በዚህ ጉዳይ የሰጡት መግለጫ ይህንኑ የሚያሳይ ነው። “ ሁሉም፤ከማዕከላዊ አፍርካ ጀምሮ ፤ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ፤ አሁን ደግሞ ጋቦን፤ አስቸጋሪ ሁኔታ ነው ፡፤ እዚያ  ምን እየሆነ ነው? ፖሊያስችችን እንዴት ማሻሻል እንችላለን፤  ይህ ሁሉ ለአውሮጳ ትልቅ የቤት ስራ ነው   

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW