1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በምዕራብ ኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር ተጽእኖ በእርዳታ አቅርቦት ላይ 

ሐሙስ፣ ጥር 26 2014

ቢሮው ባለፈው ሳምንት  ባወጣው ሪፖርት ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቁጥርም እየጨመረ መሆኑን ገልጿል። በምስራቅ፣ምዕራብ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ዜጎች እየተፈናቀሉ መሆኑን የጠቀሰው ቢሮው፣ በምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ከ250,000 በላይ ዜጎች ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያሻቸው በሪፖርቱ ጠቁሟል

Mendi city
ምስል፦ DW/N. Desalegn

የምዕራብ ኢትዮጵያ ፀጥታና የኦቻ ሥጋት

This browser does not support the audio element.

 

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታዎች ማስተባበሪያ ቢሮ በእንግሊዘኛ ምህጻሩ (ኦቻ)  የምዕራብ ኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር ሰብአዊ እርዳታ ለማቀበል እንቅፋት እንደሆነበት አስታወቀ፡፡ ቢሮው ባለፈው ሳምንት  ባወጣው ሪፖርት ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቁጥርም እየጨመረ መሆኑን ገልጿል። በምስራቅ፣ምዕራብ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ዜጎች እየተፈናቀሉ መሆኑን የጠቀሰው ቢሮው፣ በምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ከ250,000 በላይ ዜጎች ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያሻቸው በሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ በቤኒሻንጉል መተከል የነበረው አለመረጋጋት ወደ ካማሺና አሶሳ ዞን መዛመቱንና በቅርብ ደግሞ በማኦ-ኮሞ ልዩ ወረዳ የስደተኛ መጠለያ ሰፈር በታጠቁ ኃይሎች መዘረፉንም ገልጸዋል።

ነጋሳ ደሳለኝ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW