1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል

ሐሙስ፣ ኅዳር 19 2017

የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሠላምይሁን ሙላት ዝናቡ በደባርቅ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች በ500 ሄክታር ማሳ ጉዳት ማድረሱን አረጋግጠዋል። ከ600 በላይ አባዎራዎች ለችግር መዳረጋቸውንም ገልጠዋል።

700 የሚጠጉ አርሶ አደሮች ሰብላቸው መውደሙን የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል።
ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አቅራቢያ የጣለው ከባድ ዝናብ በደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ተናገሩ።ምስል Aleminew Mekonnen/DW

በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል

This browser does not support the audio element.

 

ሰሞኑን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አቅራቢያ የጣለው ከባድ ዝናብ በደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ተናገሩ። በረዶ ቀላቅሎ በጣለው በዚሁ ከባድ ዝናብ ከ700 የሚጠጉ አርሶ አደሮች ሰብላቸው መውደሙን የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል።በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አስተዳደርና አካባቢው ሰሞኑን የጣለው ከባድ ዝናብ በሰብላቸው ላይ ጉዳት ማድረሱን የአካባቢው አርሶአደሮች ተናግረዋል።

ዝናቡ በደረሱ የስንዴ፣ የቦቆሎ፣ የገብስና ሌሎች አዝርዕቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ብልዋል። ለእንሳቱ የሚሆን ቀለብ እንኳ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በመውደሙ እንሳቱም ለርሀብ መጋለጣቸውን ነው አርሶ አደሮቹ ያስረዱት።

በገብስ፣ ባቄላና ጤፍ ሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷልአረሶአደሮች

በዝናቡ ሰብላቸው ከተጎዳባቸው አርሶአደሮች መካከል አቶ ቢራራ ሁነኛው አንዱ ናቸው፣

“... የደረሰ ባቄላና ገብስ ነበረኝ፣ በጣም ጉዳተ ደርሶበታል፣ ምን ያልተጎዳ አለ፣ አገሩ በሙሉ ነው የተጎዳው” ብለዋል።

በጉዳቱ 10 ኩንታል ምርት የወደመባቸው ሌላው አርሶአደር ዝናቡ ባልተጠበቀ መንገድ ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት፡፡

ዝናቡ በደባርቅ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች በ500 ሄክታር ማሳ ጉዳት ማድረሱን የአካባቢዉ ባለሥልጣናት አስታዉቀዋልምስል Aleminew Mekonnen/DW

500 ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ ሰብል ወድሟል፣ 600 በላይ አርሶአደሮች ጉዳቱ ደርሶባቸዋል

የደባርቅ ከተማአስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በእውቀት አየነው፣ በከባድ ዝናቡ በ500 ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ ሰብል ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን በአባወራ ደረጃ 678 አርሶአደሮች ሰብላቸው ተጎድቷል ብለዋል።

የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሠላምይሁን ሙላት ዝናቡ በደባርቅ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች በ500 ሄክታር ማሳ ጉዳት ማድረሱን አረጋግጠዋል። ከ600 በላይ አባዎራዎች ለችግር መዳረጋቸውንም ገልጠዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በእውቀት አጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ባለሙያዎች መረጃዎችን እየስበሰቡ እንደሆን ተናግረዋል።

እየጣለ ያለው ዝናብ በስሜን ኢትዮጵያ ከህዳር 22/2017 በኋል ያቆማል ተብሏል

የምዕራብ አማራ አየር ትንበያ ማዕከል የትንበያ ባለሙያና ተመራማሪ አቶ መልካሙ በላይ አሁን በአማራ ክልል አልፎ አልፎ እየታየ ያለው ያልጠበቀ ዝናብ እስከ ህዳር 21/2024 ዓ ም እንደሚቀጥል ጠቁመው ከህዳር 22/2017 ዓም በኋል እንደሚያቆም ለዶይቼ ቬሌ አመልክተዋል።

በአማራ ክልል አምና በደረሰዉ የጎርፍ አደጋ በርካታ ገበሬዎች ሰብላቸዉ ወድሟል።ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋልም።ምስል South Gondar zone Disaster prevention Office/Alemnew Mekonnen/DW

በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ በርከት ባሉ ወረዳዎች በ2015/16 ዓ ም የምርት ዘመን ከ450 ሺህ በላይ ዜጎች በድርቅ ጉዳት ደርሶባቸው ቆይቷል፣ በ2016 ዓ ም ክረምት ደግሞ 3ሺህ ያክል ወገኖች በመሬት መንሸራተት ጉዳትን አስተናግደዋል፣  በደባረቅ ከተማና አካባቢው ሰሞኑነ በጣለው ከባድ ዝናብ ደግሞ ከ600 በላይ አርሶአደሮች ከ2ሺህ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለጉዳት ተዳርገዋል።

ዓለምነው መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ፀሐይ ጫኔ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW