1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሩስያ ያልታደመችበት የሰላም ጉባኤ

ሰኞ፣ ሰኔ 10 2016

በዚህ መግለጫ ፊርማቸውን ባለማስቀመጥ ተቃውሟቸውን የገለጹ አገሮች መኖራቸው ታውቋል፡፤ ከነዚህ መካከል ከእስያ ህንድ፣ ከደቡብ አሜሪካ ሜክሲኮ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ ሳኡዲ አረቢያና ከአፍሪካ ደቡብ አፍርካ ይገኙበታል።

Friedensgipfel Ukraine in der Schweiz | Ukraines Präsident Wolodymyr Selenskyj, Chiles Präsident Gabriel Boric und Kanadas Premierminister Justin Trudeau
ምስል Sean Kilpatrick/ZUMA Press/IMAGO

በሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ላይ የመከረው የሰላም ጉባኤ

This browser does not support the audio element.

ከሁለት አመት በላይ በዘለቀው የዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት ላይ የመከረውና በስዊዘርላንድ ቡርኼንስቶክ ከተማ ለሁለት ቀናት የተከሄደው የዩክሬን  የሰላም ጉባኤ ትናት ማምሻውን የጋራ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። በጉባኤው ከ 93 በላይ አገሮች፤ ሶስት የአውሮፓ ህብረት ተቋማትና ሌሎች አለማቀፍ ድርጅቶች ጭምር ተሳትፈዋል። ሩሲያ ግን ቀድሞውንም  በጉባኤው ያልተጋበዘች ሲሆን፤ ቻይና ደግሞ የሩሲያን አለመጋበዝ በምቃወም እንዳልተሳተፈች ነው የተገለጸው።
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ፣ የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ፣ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮና የብርታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ በጉባኤው ከተገኙት መሪዎች ውስጥ ናቸው። የዩክሩይኑ ፕሬዝዳንት  ቮሎደሚር ዘለንስኪ በጉባኤው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፤ አለም አንድ ላይ ከሆነ ይህንን ጦርነት በማስቆም የዓለምን ሰላም ጭምር ማረጋገጥ እንደሚችል ያላቸውን እምነት በመግለጽ፤ በጉባኤው ይህን ያህል ብዛት ያላቸው አገሮች መሳተፋቸው በራሱ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል።

በጉባኤው የተሰሙ ንግግሮችና የተላለፉ ጥሪዎች

በጉባኤው የተሳተፉ አብዛኛዎቹ  የምራብ መንግስትት መሪዎችና ተወካዮች ባሰሟቸው ንግግሮች፤ ሩሲያ ዩክሬይን ላይ ፈጽመዋለች ያሉትን ወረራ በማውገዝ፤ የዩክሬን ነጻነትና የግዛት አንድነት መከበር እንዳለበት አሳስበዋል፤ ለዩክሬን የሚሰጡቱን እርዳታም እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። የአሜሪካ  ምክትል ፕሬዝዳንት ካማሊ ሀሪስ በንግግራቸው፤ አገራቸው ዩክሬንን የምትረዳው ለዩክሬን  መደፈር በመቆጨትና ለዩክሬን ህዝብ በማዘን ብቻ ሳይሆን፤ ለራሷም ስትራቲጂካዊ ጥቅም መሆኑን ግልጽ አድርገዋል።
 የአውርፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ፎንዴርልየን በበኩላቸው ባሰሙት ንግግር፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት ያልነካው የአለም ክፍል የሌለ መሆኑን በማንሳት፣ በጦርነቱ ምክንያት የእህይል ዋጋ የናረ፣ የምግብ ዋጋ የጨመረ መሆኑን፤  ባጠቃላይም በዚህ ጦርነት የአለም ኢኮኖሚና ሰላም የተናጉ መሆናቸውን በማውሳት  “አንድ ትልቅ አገር ትንሽ ጎርቤቱን በወታደርዊ ሀይል ሊወር ይገባውልን?” ሲሉም ጠይቀዋል።

በዩክሬይን ሰላም ላይ የመከረ ዓለምአቀፍ ጉባኤምስል Michael Buholzer/REUTERS

ጉባኤው ትኩረት የሰጣቸው አጀንዳዎች
በጉባኤው  ዩክሬን ቀደም ሲል ያቀረበችው ባለ አስር ነጥብየሰላም ሀሳብ ትኩረት እንዴረግበት ተፈልጎ የነበር ቢሆንም፤ ጉባኤተኞቹ ትኩረት የሰጡባቸውና በመግለጫዎችቸውም ያነሷቸው፤ የኒውክለር ሀይል ደህንነት ፣ ዩክሬይን የምግብ ዕህልን ወደ ውጭ መላክ የምትችልበት ሁኔታና፤ የእስረኖች ልውውጥ  አጀንዳዎች እንደነበሩ ተገልጿል። ቀደም ሲል ሩሲያ ምንም እንኳ አብዛናዎቹ የጉባኤው ተሳፊ የምራብ መንግስታት ውድቅ ያደረጉት ቢሆንም፤ ለሰላማዊ ድርድር፤ ዩክሬይን የስሜን አትላንቲክ ድርጅት ኔቶ አባልነት ጥያቄዋን እንድትተውና  ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ከያዘቻቸው የዩክሬን ግዛቶች ጭምር ወታደሮቿን እንድታስወጣ የሚጠይቅ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣ ነበር።

የዩክሬይን ፕረዚደንት ቮሎደሚር ዘለንስኪምስል Sean Kilpatrick/Zumapress/IMAGO

 የጉባኤው የጋራ መግለጫ ይዘትና የተንጸባረቁ ልይነቶች
የጉባኤው ተስታፊዎች በመጨረሻ ያወጡት የጋራ መግለጫ  በጥቅሉ የአገሮች ሉኡላዊነትና ነጻነት ሊጠበቅና ሊከበር የሚገባው መሆኑን በመግለጽ  ማንኛውንም በሌላ ሉእላዊ አገር ላይ የሚቃጣንና የሚፈጸምን የሀይል እርምጃ፤ በዩክሬይን ላይ የተፈጸመውን ጨምሮ የሚያወግዝ ነው። መግለጫው  በተለይ በኒውክለር  ሀይል አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ ማደረግን፤ ወደውጭ የሚላከው የምግብ ዕህል መስተጉጓጎል የሌለበት መሆኑንና ወደ ሩሲያ የተስወሰዱ ህጻናትና ሰለማዊ ሰዎችን እንዲመለሱ የሚጠይቅ ነው።

ይሁን እንጂ በዚህ መግለጫ  ፊርማቸውን ባለማስቀመጥ ተቃውሟቸውን  የገለጹ አገሮች መኖራቸው ታውቋል፡፤ ከነዚህ መካከል ከእስያ ህንድ፣ ከደቡብ አሜሪካ ሜክሲኮ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ ሳኡዲ አረቢያና ከአፍሪካደቡብ አፍርካይገኙበታል።
የጉባኤውን ስኬትና የተፈጠሩን ልዩነቶች አስመልክቶ የጄኦፖሎቲካ ስትራቴጂስት የሆኑት ወይዘሮ  ቬሊና ትካኮሮቫ  ለዲደብሊው አለማቀፍ አገልግሎት ሲናገሩ እንደተስሙት፤ የዚህ ጉባኤ ስኬትና ጉድለት ከተለይዩ ማእዘኖች መታየት ይኖርበታል፤ “  ከዩክሬይን እንጻር ይህ ጉባኤ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ነው በሌላ በኩል በተክፋፈለ አለም ውስጥ ያለን መሆኑንም የሚያመላክት ነው” በማለት በጉባኤው መግለጫ አብዛኛዎቹ  ያልፈረሙት በአለማችን የደቡቡ ክፍል ያሉትና የብሪክስ አባል አገሮች መሆናቸውን ገልጸዋል።
ገበይው ንጉሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW