1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሩዋንዳዉ የዘርፍጅት ተፈላጊ ወደ ዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ሊዛወሩ ነዉ

ረቡዕ፣ ግንቦት 26 2012

ባለፈዉ ወር ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ በቁጥጥር ስር የዋሉት ፤ በሩዋንዳዉ የዘር ፍጅት እጃቸው እንዳለበት የሚነገርላቸው እና የርዋንዳን የዘር ፍጅት በሚመለከተው በዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ይፈለጉ የነበሩት ፍሊሲዬን ካቡጋ ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኛ ፍርድ ቤት ተላልፈዉ እንደሚሰጡ ተነገረ።

Frankreich, Paris: Anhörung von Felicien Kabuga zum Völkermord von Ruanda
ምስል picture-alliance/dpa/B. Peyrucq

ባለፈዉ ወር ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ በቁጥጥር ስር የዋሉት ፤ በሩዋንዳዉ የዘር ፍጅት እጃቸው እንዳለበት የሚነገርላቸው እና የርዋንዳን የዘር ፍጅት በሚመለከተው በዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ይፈለጉ የነበሩት ፍሊሲዬን ካቡጋ ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኛ ፍርድ ቤት ተላልፈዉ እንደሚሰጡ ተነገረ። የፈረንሳይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስተላልፈዉ ብይን የካቡጋ ጤንነት ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኛ ፍርድ ቤት እንዳይሰጡ የሚያደርግ አደለም ብሎአል። ፍርድ ቤቱ በመለጠቅ ለመንግሥታቱ ፍርድ ቤት የዝዉዉር ደብዳቤ ጽፎባቸዋል። በዘር ፍጅት እና የዘር ፍጅትን በማነሳሳት ሲፈለጉ የነበሩት የ 84 ዓመቱ ሩዋንዳዊ ፍሊሲዬን ካቡጋ ላለፉት 26 ዓመታት ገደማ ራሳቸውን ቀይረው በፈረንሳይ ያለምንም ችግር ኖረዋል። ቀደም ሲል ዩናይትድ ስቴትስ ፍሌሲየን ካቡጋ ያለበትን የጠቆመ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ወሮታ እሰጣለሁ ስትል አስታዉቃ ነበር።  

 

አዜብ ታደሰ 

ታምራት ዲንሳ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW