በራሱ ምዘና ብቻ ተማሪዎችን ለመቀበል የወሰነዉ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ
ሰኞ፣ ነሐሴ 27 2016ከአዲሱ 2017 ዓመት ጀምሮ ተማሪዎችን በብቃት ብቻ ነው የምቀበለው ሲል ዛሪ በይፋ ያስታወቀው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ የትምህርት ዘመን ተቋሙን የሚቀላቀላቀሉት ተመሪዎች በማወጣው የመመዘኛ ፈተና መሰረት በብቃት እና በችሎታ ብቻ ይሆናል ሲል አስታወቅ።ላልፍት 70 ዓመታት በሀገሪቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመሆን ሲያገለግል የቆየው አንጋፋው የአዲስ አበባ ዪንቪርስቲ ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ መሉ በሙሉ በራሱ የምዘና መስፈርት ብቻ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ዛሬ በይፋ አስታውቋዋል።
ዩንቨርስቲው እንደቀደሙው በመንግስት በኩል የሚደረግለት የተማሪዎች ምደባ አለመኖሩ የገለፀ ሲሆን የ 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች እና ትምህርት ሚንስትር ያወጣው የማለፊያ ነጥብ ማለትም ሀገራዊ ፈተናውን 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ማግኘት አንዱ መስፈርት እንዳለ ሆኖ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ሀገራዊ የማለፊያ ነጥብ እንደመነሻ በመያዝ በሚያወጣው የራሱ መመዘኛ ፈተና መሰረት አቅምና ብቃትን ብቻ መሰረት ያደረገ ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና ይሰጣል።
ይህንን ፈተና ወስደው የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ብቻ ተቁዋሙን ይቀላቀላሉ ሲሉ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሟኤል ክፍሌ ተናግረዋል ።
በቅድመ ምረቃ በ2017 መስፈርቱን የሚያሙዋሉ ከ 4500 እስከ 5000 ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውን የተናገሩት ተጠባባቂው ፕሪዝዳንት ዩንቨርሲው መክፈል የሚችሉ ተማሪዎች እና በመንግስት ድጎማ የሚደረግላቸውን ተማሪዎች ለሁሉም እኩል እድል የሚሰጥ ብቃትን እና ችሎታን ብቻ መሰረት ያደረገ የምዝገባ ሂደት እንዳለ አስታውቀዋል።
በርግጥ ይህ የምዝገባ ሄደት በወጭ መጋራት ወደተቋሙ የሚገቡ ተማሪዎች እድል ላይ የሚፈጥረው ጫና በሂደት የሚታይ ቢሆንም በዚህ አንጋፋ ተቋም መማር የሚፈልጉ እና የሀገሪቱን የከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ነጥብ ያለቸው ተማሪዎች በዩንቨርስቲውድህ-ረገፅ በመግባት ለዚሁ በተዘጋጀው ገፅ ትክክለኛ መረጃቸውን በመሙላት መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።
በተቋሙ ተመዝግበው ለመማር የሚፈልጉ የጎረቤት ሀገራትና በኢትዮጵያ ተጠልለው የሚገኙ ስደተኞችን እንደሚቀበል እንድሁም እና እነዚህ ተማሪዎች ክፍያቸውንም በተለያዩ የውጭ ምንዛሪ መፈፅም እንደሚችሉ ተገልጿል።
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እራስ ገዝ በመሆን ጎዳና ቀዳሚ ይሆን እንጂ ሌሎች የሀገሪቱ ዩንቨርስቲዎችም የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲን ፍለግ ተከትለው የሚቀጥሉ ይሆናል ተብሎዋል።
ሃና ደምሴ
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ