በርሊናሌ ፊልም ፌስቲቫል-ያልተጠበቀ ውጤት
ሰኞ፣ የካቲት 23 2001ማስታወቂያ
ከታዋቂ የሆሊውድ ብርቅዬ አርቲስቶች አንስቶ እስከ ታላላቅ የዓለማችን የፖለቲካ መሪዎች ተመላልሰውበታል፥ የበርሊኑ ቀይ ምንጣፍ። ለአስር ተከታታይ ቀናት በበርሊን ከተማ በደመቀ መልኩ ሲከበር ቆይቶ ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀው በርሊናሌ ፊልም ፌስቲቫል በስተመጨረሻ አስደናቂ ሆኖ ነበር የዋለው። በፊልሙ ዓለም ፈፅሞ የማትታወቀው የፔሩ ተወላጅ ሴት የፊልም ዳይሬክተር ክላውዲያ ሎዛ ቀዩ ምንጣፍ ላይ በብቸኝነት ተራምዳለች። በደመቀ ጭብጨባ ታጅባም “La Teta Asustada” “የወተት ሀዘን” በሚል ርዕስ ያቀረበችው ፊልሟ በአንደኝነት ተመርጦ ተሸላሚ አድርጓታል።
Sileshi,Mantegaftot,Negash Mohammed
ZPR,Agenturen