1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ተጠናክሮ የቀጠለው ውጊያ

ሥዩም ጌቱ
ሐሙስ፣ ኅዳር 17 2019

በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር አከባቢዎች ባድሜ አቅራቢያ በሚገኘው ገመሃሎና ሰንበል መሃል ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ከባድ ውጊያ እንደነበር ተነገረ። እንደ የዓይን እማኞች ከያዝነዉ ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ባድሜ ከባድ መሳሪያ ሲተኩስ ቆይቶ አሁን ወደ እግረኛ ውጊያ ገብቷል፡፡

  የባድመ ጦርነት እእአ 2005
የኤርትራ ኢትዮጵያ አወዛጋቢ ድንበር

በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ተጠናክሮ የቀጠለው ውጊያ

This browser does not support the audio element.

በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ተጠናክሮ የቀጠለው ውጊያ

በሰሜን ምዕራብ የትግራይ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አከባቢዎች ባድሜ አቅራቢያ በሚገኘው ገመሃሎ እና ሰንበል መሃል ዛሬ ሓሙስ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ከባድ ውጊያ እንደነበር ነዋረዎች አመለከቱ፡፡ እንደ የአከባቢው የዓይን እማኞች ከማክሰኞ ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ  ባድሜ ከባድ መ ሳሪያ ሲጥል ቆይቶ፤ ከትናንት ጀምሮ ደግሞ ወደ እግረኛ ውጊያ ተገብቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት መብራሪያ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ጦርነት ከገቡ አሸናፊው የታወቀ ነው ሲሉ ዝተዋል፡፡

በዓለም ዙሪያ የሚከሰቱ የፖለቲካ እና የትጥቅ ግጭቶችን መረጃ በቅጽበት በመሰብሰብ ሰንዶ የሚተነትን እና በካርታ የሚያሳየው ገለልተኛና ዓለም አቀፋዊ ተቋም የሆነው ACLED (Armed Conflict Location & Event Data Project) ትናንት ረቡዕ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም. እንዳመለከተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዋህላ-ኒቢን በመቆጣጠር ጓል ገመሃሎ የተባለውን የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አከባቢን ሲደበድብ ቆይቷል፡፡ ተቋሙ ከአከባቢው ነዋሪዎች አገኘሁ ባለው መረጃ መሰረት  የኢትዮጵያ  መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ ሰላም ኃይል ጓል-ገማሎ፣ ገዘ-ተጋሩ እና ሰምበል የተባሉ አከባቢዎችን በትናንቱ ውጊያ ተቆጣጥሯል፡፡  

የሰሜን ምዕራብ ትግራዩ የኤርትራ ድንበር አከባቢ ውጊያ

በሰሜን ምዕራባዊ የትግራይ ክልል አከባቢዎች ከሰሞኑ የታየውን ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴን ተከትሎ ከትናንት ጀምሮ ከባድ የእግረኛ ውጊያ መከሰቱን ለዶይቼ ቬለ የገለጹት የአከባቢው ነዋሪዎች በፊናቸው፤ ከትናንት እረቡዕ አመሻሽ ጀምሮ ዛሬም ሓሙስ ውጊው በከባድ የተኩስ ልውውጥ ቀጥሎ ተጨማሪ ኃይልም ወደ አከባቢው እየደረሰ ነው ብለዋል፡፡ አስተያየታቸውን የተጠየቁት የሽራሮ አከባቢ የዓይን እማኝ፤ እንዳመለከቱት “ያው ውጊው እንደቀጠለ ነው፤ ሌሊቱን በሙሉ ውጊያ ነበር” በማለት ተጨማሪ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ ስፍራው እየገባም ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡ “ከሽራሮ ተከዘ ወደ ባድሜ አቅጣጫ ውጊያው ጠንከር ብሎ አድሯል” ሲሉ የገለጹት አስተያየት ሰጪ የአከባቢው ነዋሪ፤ አከባቢው ሌሊቱን በሙሉ በድሮን ሲመታም እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ አስተያየት ሰጪው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና አጋሮቹ ገማሃሎን አልፈው ወደ ሰንበል አከባቢ ውጊ እያደረጉ ነው በማለት ይህ በገመሃሎና ሰንበር መሃል የሚደረገው ውጊያ ሌሊቱን አንግቶ አሁንም እንደቀጠለ ነው ብለዋል፡፡

ያሰጋው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ውዝግብ

በኢትዮጵያ የውስጥ ችግር ላይ እጇን በማስገባት በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የምትከሰሰው ኤርትራ በዚህ ውጊያ ውስጥ ስለመሳተፏ ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ፡፡ ዛሬ ሓሙስ በተካሄደው የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ወቅትም ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጥያቄ ያቀረቡ የምክር ቤቱ አባላት በዚህ ረገድ ያለባቸውን ስጋት ገልጸው ስለመንግስት ዘድግጁነት ጠይቀዋል፡፡ ጥያቄውን ያቀረቡት አንደኛው የምክር ቤቱ አባል፤ “የሉዓላዊነታችን ዋስትና የመከላከያ ሠራዊታችንን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማጠናከር ነው” በማለት ጥቃትን አስቀድሞ የሚመክት የመከላከያ ሠራዊት በመገንባት የአገሪቱ ሉዓላዊነት እንዳይደፈር ከማድረግ አኳያ ስላለው ዝግጁነት ጠይቀዋል፡፡

ስለ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ውጥረት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት  ማብራሪያም ስለ አሁናዊው የኤርትራ ድንበር ውጊያ እና ስለሚካሄደው ግጭት በቀጥታ ማብራሪያ ባይሰጡም፤ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ስላሉበት ተቃርኖ ግን አልሸሸጉም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመውረር እየሰራች ነው በሚል የሚቀርበውን ክስም አጣጥለው፤ ኢትዮጵያ  ከኤርትራ በወቅቱ የምትፈልፈው ይህ ነው ብለዋል፡፡ “ከኤርትራ የምንፈልገው ሁለት ነገር ነው፤ አንድ የኢትዮጵያ ጠላት ማስታጠቂያ መስመር መሆን ማቆም ሲሆን ሁለት ለጋራ ልማት አብራችሁን ቁሙ ተባባሪ ሁኑ” በማለት ሻቢያ ያሉት የኤርትራ መንግስት ግን “በማይታረም ስህተት ውስጥ የሚዳክር ኃይል ከሆነ ጥፋቱ ለኤርትራ ነው የሚሆነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “ስለ ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምሁራን ስተው ነበር” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን በማንቃት ላይ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ያለውም ፍላቆት “መዝረፍ መቀማት” ሳይሆን አብረን ማደግ ነው በማለት ለትብብር ጠይቀዋል፡፡ በምድርም በሰማይም ተዘግተን ሰላም የሚሆን ቀጣና የለም ብለዋልም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ስለሻከረው የኢትዮጵያ እና ኤርትራግንኙነት በሰጡትም ማብራሪያ ጦርነቱ ከተጀመረ አሸናፊው የታወቀ ነው ሲሉ ዝተዋል፡፡ “ከተገባ የሚያግዝህ የለም፤ እራስህ ነው የምትሸከመው፡፡ ማንም አይሞትልህም” በማለት ለኤርትራ ግን ከኢትዮጵያ ማንም እንደማይቀርባት አብራርተዋል፡፡ ከኤርትራ ጋር “ውጊያ ከተጀመረ ምንም ትርትር የለውም ኢትዮጵያ አሸናፊ ናት” ያሉት ዐቢይ “እደመራለሁ ያለ ኃይም ካለ ለዛ ነው ዝግጅታችን” በማለት አብራርተዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

Edited by: Negash Mohammed ነጋሽ መሐመድ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW