1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስኢትዮጵያ

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ቪዲዮዎችን እንዴት መለየት ይቻላል?

ረቡዕ፣ ግንቦት 28 2016

በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በመታገዝ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም /ቪዲዮዎች/ መስራት በአሁኑ ወቅት እየተለመደ መጥቷል። እነዚህ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ሰዎች ያልሰሩትን እና ያላሉትን ነገር እንዳሉ እና እንደሰሩ ተደርጎ የሚቀርብ በመሆኑ የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃዎችንም ያስፋፋሉ። ታዲያ እነዚህን ቪዲዮዎችን እንዴት መለየት ይቻላል?

ዲፕፌክ የሚባለውን የሰውሰራሽ አስተውሎትን መተግበሪያ በመጠቀም የእውነት የሚመስሉ ነገር ግን ሐሰተኛ የሆኑ ምሥሎችን እና ቪዲዮዎችም እየተሰሩ ነው።በዚህ ቴክኖሎጂ የአንድን ሰው ፎቶ እና ቪዲዮ በሌላ በመተካት እውነት  በሚመስል መልኩም ተቀናብሮ ይሰራል።
ዲፕፌክ የሚባለውን የሰውሰራሽ አስተውሎትን መተግበሪያ በመጠቀም የእውነት የሚመስሉ ነገር ግን ሐሰተኛ የሆኑ ምሥሎችን እና ቪዲዮዎችም እየተሰሩ ነው።በዚህ ቴክኖሎጂ የአንድን ሰው ፎቶ እና ቪዲዮ በሌላ በመተካት እውነት በሚመስል መልኩም ተቀናብሮ ይሰራል።ምስል DW

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ቪዲዮዎችን እንዴት መለየት ይቻላል?

This browser does not support the audio element.

እውነተኛ የሚመስል ቪዲዮ ተመልክተው ነገር ግን በደንብ ሲጠና ቪዲዮው የሰውሰራሽ አስተውሎት ፈጠራ ሆኖ አግኝተውት ያውቃሉ? በእርግጥ የሰውሰራሽ አስተውሎት ፈጠራ እውነታ ላይ ያለንን ግንዛቤ ይፈትናል። የዛሬው የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዝግጅት በሰው ሰራሽ አስተውሎት በሚሰሩ ቪዲዮዎችን እንዴት መለየት እንደምንችል ጥቆማ ይሰጣል።

ባለንበት የዲጅታል ዘመን እጅግ በረቀቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶች  አማካኝነት እውነት የሚመስሉ ግን እውነት ያልሆኑ ነገሮች ተቀነባብረው ሲቀርቡ ይታያል። በተለይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በመታገዝ እንደ ሥነ ጽሑፍ፣ ሙዚቃ እና ግጥምን የመሳሰሉ የሥነ ጥበብ ስራዎችን መስራት በአሁኑ ወቅት እየተለመደ መጥቷል።ከዚህ ባሻገር በዚህ ቴክኖሎጅ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም /ቪዲዮዎች/ በፈጠራ መልክ ይዘጋጃሉ። እነዚህ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ከእውነተኛዎቹ  ጋር በጣም የተቀራረቡ በመሆናቸው ደግሞ  በጥንቃቄ  መመርመር  ካልቻልን በስተቀር ለመለየት አስቸጋሪ ናቸው።
በዚህ የተነሳ አንዳንዶች ሀሰተኛ ይዘቶችን በማሰራጨት ይህንን ቴክኖሎጂ ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙበት ይታያል።ሰው ሰራሽ አስተውሎት የመጭው ዘመን ፈተና

በስዊዘርላንድ የሶፍትዌር ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳዊት ዓለሙ  እንደሚሉት፤ እነዚህ የፈጠራ ቪዲዎች በሁለት መንገድ ይዘጋጃሉ።የመጀመሪያው ዲፕ ፌክ የሚባለው እና ከእውነተኛ ነገር በመነሳት የሚሰራው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰራ ፈጠራ  ነው።

አቶ ዳዊት ዓለሙ የሶፍትዌር መሀንዲስምስል Privat

በዚህ ሁኔታ «ዲፕፌክ »የአንድን ሰው ቪዲዮ በመውሰድ የሰውየው ድምፅ እንዲሁም ሲናገር የሚያሳየውን የዓይን አገላለጥ፣ የእጅ፣ የአንገት እና የከንፈር እንቅስቃሴ የመሳሰሉትን አካላዊ  ሁኔታዎች ለማሽን በማስጠናት፤ ከዚያም የምንፈልገውን  ይዘት እውነተኛ በሚመስል መልኩ በመተካት  ዲጂታል በሆነ መንገድ  ተቀነባብሮ የሚሰራ  ነው። ከዚህ አንፃር  ቪዲዮው ለእውነታ የቀረበ በመሆኑ፤ አቶ ዳዊት እንደሚሉት የበለጠ አደገኛ ነው። 
በዚህ መንገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታዋቂ ሰዎችን ድምፅ እና አካላዊ ቁመና በማቀናበር የፈጠራ ቪዲዮ እየተሰራ ሲሆን፤ በቅርቡ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዶናልድ ትራምፕን ሲሳደቡ  የሚያሳየው የሀሰት ቪዲዮ ተጠቃሽ ነው። ሰውሰራሽ አስተውሎትና ሐሰተኛ ወሬዎች

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዚህ ቴክኖሎጅ ተቀናብረው በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከሚሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች  መካከል አብዛኞቹ ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ሲሆኑ ፤  99 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው።በዚህ መንገድ ከሁለተኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ እስከ ሚታወቁ ሴቶች  ዒላማ የተደረጉ ሲሆን፤ የችግሩ ሰለቫ ከሆኑ ታዋቂ ሴቶች መካከልም ዝነኛዋ ድምጻዊት ቴይለር ስዊፍት እና  የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚንስትር  ጆርጂያ ሜሎኒ  ይጠቀሳሉ።
በሌላ በኩል በእነዚህ የፈጠራ ቪዲዮዎች ሰዎች ያልሰሩትን እና ያላሉትን ነገር እንዳሉ እና እንደሰሩ ተደርጎ የሚቀርብ በመሆኑ  የጥላቻ ንግግር እና  ሀሰተኛ መረጃዎችንም ያስፋፋል። ይህም በተለይ ምርጫ  በሚደረግባቸው እና ግጭት ባለባቸው  ሀገሮች ችግሩን ሊያሰፋው እና በህብረተሰቡ ላይ ከባድ አደጋ ሊፈጥር ይችላል።ዲሞክራሲንም አደጋ ላይ የመጣሉ ዕድል ከፍተኛ ይሆናል። ይህም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ብዙ ተቃርኖ ባለበት ሀገር ችግሩን የበለጠ ያባብሳል። 

ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በአሁኑ ወቅት የሰው ልጆችን የዕለት ተዕለት ህይወት በአወንታዊም ይሁን በአሉታዊ መልኩ እየለወጠ ነው።ምስል DW

እንደ አቶ ዳዊት ቴክኖሎጂው እያደገ የሚሄድ በመሆኑ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ባይሆኑም ለጊዜውም ቢሆን እውነተኛ አለመሆናቸውን መለየት የሚያስችሉ ምልክቶች መኖራቸውን ይገልፃሉ።
ከዚህ ባሻገር ቪዲዮዎችን የሚለዩ ድረ-ገጾች  ላይ የተንቀሳቃሽ ምስሉን መገኛ አድራሻን በማስገባት ወይም ቪዲዮውን በመጫን ፍተሻ ማድረግ ይቻላል።
ከዲፕ ፌክ ባሻገር በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩትን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመለየት ደግሞ ፤ገፅታቸው ላይ የሚያርፍ ብርሃን እና ጥላን መመልከት ያስፈልጋል።በእነዚህ ቪዲዮዎች ተፈጥሮዊ ያልሆነ ቀለም ፣ገፅታ እና  ቅርፅም ሊታይ ይችላል።ለምሳሌ በቪዲዮው በሚታየው ሰው የእጅ ጣት አምስት በመሆን ፋንታ አራት ጣት ብቻ ሊኖረው ይችላል።ይህም ማሽኑን ለማስልጠን ከሚሰጠው ስልተቀመር / Algorithim/ጋር በተያያዘ የሚፈጠር ችግር መሆኑን ባለሙያው ገልፀዋል።የሰውሰራሽ አስተውሎትን አጠቃቀም የሚቆጣጠሩ ህግ እና መመሪያዎች

በዚህ ቴክኖሎጂ የሰዎችን አካላዊ  ሁኔታዎች ለማሽን በማስጠናት፤ ከዚያም የምንፈልገውን  ይዘት እውነተኛ በሚመስል መልኩ በመተካት  ዲጂታል በሆነ መንገድ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን መፍጠር ይቻላል።ምስል Alexander Limbach/Zoonar/picture alliance

በአጠቃላይ በዚህ ሁኔታ የሚቀናበሩ ቪዲዮዎች «ማየት ማመን ነው» የሚለውን አባባል ዋጋ የሚያሳጡ በመሆናቸው ከማየት ባለፈ  ምክንያታዊ ሆኖ በጥሞና መመርመርን ይጠይቃሉ።ስለሆነም በማህበረሰቡ ዘንድ ምክንያታዊ አስተሳሰብን ማዳበር ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ መሆኑን ባለሙያው  ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል እነዚህ የፈጠራ ቪዲዮዎች ሁል ጊዜ ለክፉ ዓላማ ብቻ ሳይሆን፤ ለመዝናኛ፣ለህግ ፣ለትምህርታዊ እና ለህክምና አገልግሎትም ይውላሉ። ነገር ግን ይህ ቴክኖሎጂ በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ አላግባብ የመጠቀም እድልን በመስጠት የተሳሳተ መረጃ  እና የጥላቻ ንግግርን በማሰራጨት የሥነ-ምግባር ጉድለትን  ያስከትላል።በመሆኑም የዚህን ቴክኖሎጂ አላግባብ የመጠቀም አቅሙን ለመገደብ ህብረተሰቡን ማስተማር ፣ እነዚህን የፈጠራ ቪዲዮዎች የሚለዩ ቴክኖሎጅዎችን መስራት እና ቴክኖሎጅውን የሚቆጣጠር ህግና መመሪያ ማውጣት እንደ መፍትሄ ይጠቀሳሉ።አቶ ዳዊት በሃሳቡ ይስማማሉ በተለይ ወጣቶችን በማስተማር።

 

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ፀሀይ ጫኔ
ሽዋዬ ለገሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW