1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በሲዳማ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ ድንበር ሥለተደረገዉ ግጭት የሲዳማ ምስራቃዊ ዞን ምላሽ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 1 2017

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ እና ሓሙስ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን እና የሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ኮኮሳ ወረዳ እና የሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ቡራ ወረዳ በሚዋሰኑባቸው ሁለት ቀበሌያት በተነሳው ግጭት የሰው ህይወት ማለፉ እንዲሁም ሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ተነግሯል፡፡

በኦሮሞና በሲዳማ ብሔሮች ተወላጆች መካከል ባለፈዉ ሳምንት ግጭት ከተቀሰቀሰባቸዉ አካባቢዎች አንዱ።በሁለቱ ወገኖች መካከል በተነሳዉ ግጭት የሰዉ ሕይወትና ንብረት መጥፋቱ ተነግሯል።የሟቾቹ ቁጥርና የንብረቱ መጠን ግን በይፋ አልተነገረም
በኦሮሞና በሲዳማ ብሔሮች ተወላጆች መካከል ባለፈዉ ሳምንት ግጭት ከተቀሰቀሰባቸዉ አካባቢዎች አንዱ።በሁለቱ ወገኖች መካከል በተነሳዉ ግጭት የሰዉ ሕይወትና ንብረት መጥፋቱ ተነግሯል።የሟቾቹ ቁጥርና የንብረቱ መጠን ግን በይፋ አልተነገረምምስል፦ Seyoum Getu/DW

በሲዳማ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ ድንበር ሥለተደረገዉ ግጭት የሲዳማ ምስራቃዊ ዞን ምላሽ

This browser does not support the audio element.


በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልሎች አዋሳኝ አከባቢሰሞኑ የተቀሰቀሰዉ ግጭት በግለሰቦች ጠብ የተነሳ እንጂ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ የቀሰቀሰዉ እንዳልሆነ የሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን አስታወቀ፡፡የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛቸው ኖኦራ ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት ግጭቱን በዘላቂነት ለማስወገድም የሁለቱ ዞኖች እና ክልሎች ባለሥልጣናት እየጣሩ ነው፡፡ባለፈዉ ሳምንት በተደረገዉ ግጭት ሰዎች ተገድለዋል።

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሃምሌ 23 እና ሓሙስ ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ነንሰቦ ወረዳ እና የሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ቤንሳ ወረዳ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ኮኮሳ ወረዳ እና የሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ቡራ ወረዳ በሚዋሰኑባቸው ሁለት ቀበሌያት በተነሳው ግጭት የሰው ህይወት ማለፉ እንዲሁም ሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ተነግሯል፡፡

እነዚህ አከባቢዎች የሁለቱ ክልሎች ተወላጆች ተጋብተውና ተቀላቅለው የሚኖሩባቸው አከባቢ ነው የሚሉት የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛቸው ኖኦራ፤ ሰሞኑን ጨምሮ ላለፉት ጢቂት ዓመታት በዚህ አከባቢ ተከታትሎ የሚነሳው ግጭት መንስኤው የወሰን ውዝግብ አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡ “ይህ መሬት የኔ ነው በሚል የሚነሳ የመሬት ግጭት በአከባቢው የለም” ያሉት የዞን አስተዳዳሪው የግጭቱ መንስኤ ያሉትን ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ የተፈጠረውን የዚህ አከባቢ ግጭት መንስኤን ስያስረዱም በኦሮሚያ ክልል የአስተዳዳር ወሰን ውስጥ በህጋዊ ነዋሪነት በርካ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በሰላም ቢኖሩም፤ በተጨማሪነት ግን ህጋዊ የነዋሪነት ፍቃድ የሌላቸው 14 ሰዎች በአከባቢው ከግለሰቦች ጋር በገቡበት ግጭት ምክንያት ጉዳዩ ተወሳስቦ ቆይቷል ነው ያሉት፡፡ በአከባቢው ማህበረሰብ ሽምግልና ያልተፈታውን ይህን ጉዳይ ወደ ኮኮሳ ወረዳ ፍርድ ቤት የወሰዱ አራት የአከባቢው ነዋሪዎች በፍርድ ቤት እልባት ቢያገኙም በወቅቱ የሁለቱ ዞን አመራሮች ጉዳዩን በይደር ማሳደራቸውን ጠቁመዋልም፡፡
እንደ ሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪው አቶ ግዛቸው አስተያየት፤ በወቅቱም የሁለት ግለሰቦችን ጥል ወደ ጎን ያለው የአከባቢው ማህበረሰብ ጉዳዩን በእርቅ ቢያልፉትም በተለይም በ2014 ዓ.ም. ጉዳዩ ዳግም በማገርሸቱ በግጭት የሰዎች ህይወት ለማለፍም ምክንያት ሆነ፡፡ ባለፈው ሳምንት ስለተፈጠረውም ግጭት ስገልጹ፤ “ይህ ውሎ ያደረ ችግር ባለፈው ሳምንት በሁለት ግለሰቦች መሃል ግጭት በመፍጠሩ” በሁለቱም ወገኖች በኩል የሰው ህይወት ስለማለፉም ገለጸው የአገር መከላከያ ሰራዊት መሃል ገብቶ ግጭቱን ስለማብረዱም አስረድተውናል፡፡ የሁለቱ አዋሳኝ ዞኖች ሃላፊዎች ይህን ተከትሎ ዓርብ ለታ ማህበረሰቡን ባወያዩበትም ወቅት “የ14 ሰዎች ጉዳይን እልባት መስጠት ግጭቱን በዘላቂነት ይፈታዋል” ሲሉ ችግሩ የአስተዳደር ወሰን ውዝግብ አለመሆኑን አስምረውበታል፡፡በሰሞነኛው ግጭቱ ከሁለቱም ወገኖች የሰው ህይወት ማለፉንና የቆሰሉም መኖራቸውን የገለጹት አቶ ግዛቸው፤ የተጎጂዎችን ቁጥር ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል፡፡ ሆኖም ከባለፈው ዐርብ ጀምሮ ከምዕራብ አርሲ ዞን አቻቸው ጋር በጉዳዩ ላይ መምከራቸውንና የሁለቱ ክልሎች አመፈራሮች በተገኙበት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እቅድ መያዙንም ገልጸዋል፡፡ “ጉዳዩን ባለፈው ቅዳሜ ገምግመን ስህተት ነው ብለናል” ያሉት ኃላፊው፤ በ14 ሰዎች ምክንያት 100 ሺዎች መቸገር የለባቸውም በሚል የፊታችን ቅዳሜ በሁለቱ ክልሎች እና የዞን አመራሮች በተገኙበት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት አመራሩ ሃላፊነት መውሰድ እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡ 
ዶይቼ ቬለ በትናንትናው እለት ያነጋገራቸው የምዕራብ አርሲ ዞንሰላምን ፀጥታ አስተዳደር ኃላፊ አቶ ገነሙ በሪሶ፤ የዚህ አከባቢ ግጭት መንስኤ ከሲዳማ ወደ ኦሮሚያ ክልል መጥተው ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የሚኖሩ ሰዎች ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ በፍርድ ቤት ውሳኔ ብያገኝም ግለሰቦቹ ችግሩን በሃይል ለመፍታት መሞከራቸው ነው ብለዋል፡፡ የአከባቢው የግጭቱ ተጎጂዎች ዘላቂ እልባት ባለማግኘት መማረራቸውን እንዲሁም ኃላፊው ችግሩን እልባት ለመስጠት የሁለቱ ዞኖች አመራሮች እየተወያዩበት መሆኑንም ትናንት መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 
ሥዩም ጌቱ

በኦሮሚያና በሲዳማ ክልልሎች ነዋሪዎች መካከል ግጭት ከተደረገባቸዉ አካባቢዎች አንዱ።የግጭቱ ምክንያት የግዛት ይገባኛል ጥያቄ አንዳልሆነ የምሥራቅ ሲዳማ ዞን አስታዉቋልምስል፦ Seyoum Getu/DW

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

    
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW