1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሳኡዲ እስር ቤቶች የኢትዮጵያውያን ስቃይ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 28 2014

በሳዑዲ  እስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለረሃብ፣ እብደትና ሞት እየተዳረጉ እንደሆን የዓይን እማኞች ተናገሩ። ምግብ በቀን አንዴ እየተሰጣቸው በአንድ ክፍል ከ 200 እስከ 400 ታጉረው እየተሰቃዩ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ መከራ እንዲያወጣቸዉ ጠይቀዋል። የመንግሥት ባለሥልጣናትን ግን በስልክ ማግኘት አልቻልንም። 

Saudi Arabien I Äthiopische Migranten werden in ihr Herkunftsland zurückgebracht
ምስል Minasse Wondimu Hailu/AA/picture alliance

በሳኡዲ የኢትዮጵያውያን ስሞታ

This browser does not support the audio element.

ሳዑዲ አረቢያ  እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለረሃብ፣ እብደትና ሞት እየተዳረጉ እንደሆን የዓይን እማኞች ለዶቸ ቬለ ተናግረዋል። አቶ ኡመር ዳውድ በሳዑዲ አረቢያ ከአስር አመታት በላይ ኖረዋል። ከእስር ቤት ውጪ  ያዩትንና እስር ቤት ላይ በኢትዮጵያውያን ላይ ደረሰ ያሉትን ሲያስርዱ በህክምና ውስጥ የነበረች እርጉዝ የምግብ መርፌ ነቅለው ጭምር እንዳሰርዋትና በርካታ ኢትዮጵያውያን በአንድ ክፍል እስክ 200 ድረስ ታጭቀው እንደሚገኙ ገልዋል። ወይዘሮ ሣባ ገብረ ሥላሴ በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን መብት ተከራካሪ ናቸው። እስር ቤቶች ዉስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ነው ያሉት በደል «ለሰሚ ግራ የሚያጋባ ነው» ይላሉ። በአንድ ክፍል ከ200 በላይ በቀን አንዴ ብቻ ምግብ እየተስጣችው የቆሻሻ መጣያ ፕላስቲክ ደርበው እንደሚተኙ በምሬት ተናግረዋል። ወይዘሮ ሣባ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ደረሰ ያሉትን ስቃይ ጂዳ ላለው የኢትዮጵያ ቆንስላም ሆነ የዲያስፖራ ጽሕፈት ቤት «አቤት» ለማለት ሲሄዱም በራቸው ዝግ  መሆኑን ያስረዳሉ።


ሕጋዊውም ሕገወጡም ሁሉም ኢትዮጵያዊ  በሙሉ እንደሚታፈስ የገለጹልን አንድ ሌላ ስማችው እንዲጠቅስ ያልፈሉጉ ነዋሪ ደግሞ አሻራ አሳይተው ሲመለሱም ድጋሚ መንገድ ላይ እንደሚያዙና እንግልት እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል። አያይዘውም ከታሳሪዎች ታሞባቸው ሀክምና እንዲያገኝ ሲጠይቁ በእስር ቤት ጠባቂዎች እንደሚደበደቡ ገልጸዋል።
ወይዘሮ ሣባም በእስር ቤት የኢትዮጵያውያኑ አያያዝ አስከፊ እንደሆነ ያስረዳሉ። በጉዳዩ ላይ በጂዳ-ሳዑዲ አረብያ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላና የዳያስፖራ ጽሕፈ ቤት እንዲሁም የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW