በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት ይቁም!17 ኅዳር 2001ረቡዕ፣ ኅዳር 17 2001አሉአል ኮች ገና የ13ዓመት ታዳጊ ሳለች ነዉ በነፍጥ መግደልን የተማረችዉ። የደቡብና ሰሜን ሱዳን ዘመን ያስቆጠረ የእርስ በርስ ጦርነት የወለዳት የጫቃ ሽምቅ ተዋጊ።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግበህግ አምላክ!ምስል dpaማስታወቂያአሁን 36ዓመቷ ሲሆን ከመንግስት ወታደሮች ጋ ስትዋጋ ያሳለፈችዉን ሰቆቃ ስታስታዉስ ትንሽም ስቅጥጥ አይላትም። ይልቁንም ባሏ የሞተባት ኮች አሁን ቤተሰቧን ለመደገፍ የምታደርገዉን ትግል ስትናገር እንባዋ ባይኗ ግጥም ይላል።