በስልጤ ዞን የአብያተ ክርስትያናት መቃጠል
ዓርብ፣ ሚያዝያ 21 2014ማስታወቂያ
በስልጤ ዞን በሃይማኖት ተቋማት ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እስከ ዐሥራ አምስት በሚደረሱ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ አንዳሉት በቡድን የተሰባሰቡ ሰዎች በዞኑ በወራቤ ከተማ እና በሳንኩራ ወረዳ ላይ ቢያንስ ሦስት አብያተ ክርስትያናትን ማቃጠላቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የስልጤ ዞን መስተዳድር የሥራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ጉዳዩን በማጣራት ሂደት ላይ በመሆናችው ዝርዝር መረጃ መስጠት ባይችሉም ኅብረተሰቡን በማወያይት የማረጋጋት ሥራ በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ