በስደተኞች ጉዳይ ያልተግባባዉ የጀርመን ጣምራ መንግሥት
ዓርብ፣ ኅዳር 3 2008ማስታወቂያ
ወደ መሃል አዉሮጳ የሚተመዉን ስደተኛ ለመግታት በምዕራብ በኩል ስሎቬንያ ድንበርዋን ዘግታለች። ስዊድንም ትናንት የድንበር ቁጥጥር ጀምራለች። ከባልካን ሃገራት ተነስተዉ ጀርመንን አቋርጠዉ ወደ ስዊድን ይገባሉ የተባሉ አንዳንድ ስደተኞች ሰሜን ጀርመን እንዳይቀሩም አስግቷል። እነዚህ ስደተኞች በቁጥር 200 ሺህ እንደሚሆኑ ነዉ የተገመተዉ። የጀርመን የጣምራ መንግሥት በስደተኞች ጉዳይ የተፈጠረውን አለመግባባት በተመለከተ የበርሊኑ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ