1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶማሌ ክልል የጎርፍ መጥለቅለቅ ፤ ድሬ ዳዋ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ተከስተዋል

ሐሙስ፣ ነሐሴ 2 2016

በሶማሌ ክልል በዋቢ ሸቤሌ ወንዝ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ ጉዳት ሶስት ሺ የሚጠጉ ሰዎች ከመኖርያ ቀዬ መፈናቀላቸውን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ገለጠ። በሌላ በኩል በድሬደዋ አስተዳደር ሁሉል ሞጆ በተባለ የገጠር ቀበሌ ተከሰተ በተባለ የመሬት መንሸራተት የመኖርያ ቤቶች መፍረሳቸው ተገልጧል።

Äthiopien I Illegaler Menschenhandel in Amhara verringert
ምስል Somali regional state & Dire Dawa city Communication

በሶማሌ ክልል የጎርፍ እንዲሁም በድሬዳዋ የመሬት መንሸራተት ጉዳት አድርሰዋል

This browser does not support the audio element.

በሶማሌ ክልል በዋቢ ሸቤሌ ወንዝ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ ጉዳት ሶስት ሺ የሚጠጉ ሰዎች ከመኖርያ ቀዬ መፈናቀላቸውን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ገለጠ።

በሌላ በኩል በድሬደዋ አስተዳደር ሁሉል ሞጆ በተባለ የገጠር ቀበሌ ተከሰተ በተባለ የመሬት መንሸራተት የመኖርያ ቤቶች መፍረሳቸው ተገልጧል።

የብሔራዊ ሜትሮሎጂ በበኩሉ በቀጣዮቹ ጊዜያት በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዝናቡ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀጥል በመግለፅ በአካባቢዎቹ ጉዳት እንዳያስከትል የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝቧል። 

 

የጎርፍ አደጋ የሚያሰጋቸው የአፋር፣የአማራ፣የኦሮሚያ፣የሶማሊና ደቡብ ክልሎች

 

በሶማሌ ክልል የደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ 

የሶማሌ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱቃድር ረሺድ ለዶይቼ በስልክ በሰጡት መረጃ ወንዙ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ሶስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን በአሁ ሰዓት የእለት ደራሽ ድጋፍ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

ሶማሌ ክልል ሼቤሌ ዞን የጎርፍ መጥለቅለቅ ብርቱ ጉዳት

በሶማሌ ክልል በዋቢ ሸቤሌ ወንዝ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ ጉዳት ሶስት ሺ የሚጠጉ ሰዎች ከመኖርያ ቀዬ መፈናቀላቸውን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ገለጠምስል Somali regional state & Dire Dawa city Communication

 

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞንም ተመሳሳይ አደጋ ደርሷል

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ተከስቷል የተባለው ጎርፍ በዋነኛነት በእርሻ ላይ ጉዳት ማድረሱን ኃላፊው ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል በድሬደዋ አስተዳደር ሁሉል ሞጆ በተባለ ገጠር ቀበሌ ደረሰ በተባለ የመሬት መንሸራተት ሃምሳ ያህል ቤቶች መፍረሳቸውን እና በእርሻ ላይ ጉዳት መድረሱን የመስተዳድሩ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል ።

በድሬደዋ አስተዳደር ሁሉል ሞጆ በተባለ ገጠር ቀበሌ ደረሰ በተባለ የመሬት መንሸራተት ሃምሳ ያህል ቤቶች ፈርሰዋልምስል Somali regional state & Dire Dawa city Communication

 

የድሬዳዋ የጎርፍ አደጋ

በብሔራዊ ሜትሮሎጂ የሶማሌ ክልል እና አካባቢው የትንበያ ባለሞያ የሆኑት አቶ ገዳሙ ጌትነት ድሬደዋን ጨምሮ በምስራቁ ክፍል ባሉ ክልሎች በቀጣዮቹ ጊዜያት የዝናቡ መጠን ከፍ ብሎ እንደሚቀጥል በመግለፅ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ከወራት በፊት የዋቢ ሸበሌ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በበርካታ የወንዙ ዳርቻ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን መዘገባችን ይታወሳል።

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW