በሶርያ የቀጠለው የኃይል ተግባር
ሐሙስ፣ ነሐሴ 5 2003ማስታወቂያ
እንደሚታወሰው ምክር ቤቱ ቀደም ባለ ጊዚያት በዚህችው ሀገር በመካሄድ ላይ ያለውን የኃይል ተግባር አውግዞዋል። የዐረብ ሀገሮችም የሶርያ ፕሬዚደንት በሺር አል አሳድ የኃይሉን ተግባር እንዲያቆሙና የተሀድሶውን ለውጥ ባፋጣኝ እንዲያስተዋውቁ እያሳሰቡ ነው። የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱን ሶርያን ካወገዘበት ርምጃ የተቆጠበው የሊባኖስ መንግስት አቋምን የተቃወመው የሊባኖስ ህዝብ ለሶርያ ዜጎች ያለውን ድጋፍ አደባባይ በመውጣት ገልጾዋል። ይህ በዚህ እንዳለ የሶርያ መንግስት ጦር ኃይላት ዛሬም በወሰዱት ርምጃ በቢኒሽ ከተማ አራት ሰዎች መግደላቸውን የመብት ተሟጋቾች አስታውቀዋል።
ነቢዩ ሲራክ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሰ