በቄለም ወለጋ ሶስት ሳምንታትን የተሻገረው የውሃና መብራት መቋረጥ
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 2 2013
ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ለሶስት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ከትናንት ጀምሮ መመለሱን የአካባቢው ባለስልጣናት አረጋግጠዋል፡፡
በዞኑ ለሶስት ሳምንታት የዘለቀው የመብራት እና ውሃ መቋረጥ የገጠመው ከጋምቤላ ክልል የሚመጣው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር በታጣቂዎች በመቆረጡ ነው ተብሏል፡፡
የዞኑ ፀጥታ እና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ በተለይ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት መስመሩ ለሶስት ሳምንታት ሳይጠገን ተቋርጦ የቆየው በፀጥታ ሃይሎች በአካባቢው ሳይደርሱ በመቆየታቸው ነው፡፡በአካባቢው ታጥቆ ይንቀሳቀሳል የተባለው ሸማቂ ቡድን የመብራት ኃይል ሰራተኞች ላይ እገታ መፈጸሙንም ባለስልጣናቱ ተናግረዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ