1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በቆቦና አካባቢው ውጊያ መቀጠሉ

ሰኞ፣ ነሐሴ 23 2014

ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የህወሓት ታጣቂዎች ዛሬም በቆቦና ዙሪያው በከባድ ውጊያ ላይ መሆናቸውን ወልዲያ ከተማ የሚገኙ አዲስ ተፈናቃዮች ተናገሩ። ህወሓት ቆቦን ለቅቆ ወጥቷል የተባለውም እስከ ዛሬ ቀትር ድረስ ሐሰት መሆኑንም ተፈናቃዮቹ ገልጠዋል፡፡

Äthiopien | Norden | Rebellen Tigray
ምስል፦ S.Getu/DW

«ቆቦ ከተማ አልተለቀቀችም»

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የህወሓት ታጣቂዎች ዛሬም በቆቦና ዙሪያው በከባድ ውጊያ ላይ መሆናቸውን ወልዲያ ከተማ የሚገኙ አዲስ ተፈናቃዮች ተናገሩ። ህወሓት ቆቦን ለቅቆ ወጥቷል የተባለውም እስከ ዛሬ ቀትር ድረስ ሐሰት መሆኑንም ተፈናቃዮቹ ገልጠዋል፡፡ በተቃራኒው የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች በስፋት ከተማዋን እየለቀቁ ወደ ወልዲያና አካባቢው ከተሞች መድረሳቸውን ፤ የአካባቢው ጦርነትም በወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች ላይም ሥጋት መፍጠሩን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። 

ባለፈው ነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓም እንደገና ያገረሸው የሰሜኑ ጦርነት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ዙሪያ መቀጠሉን፣ በቆቦ ከተማ ደግሞ ዝርፊያ መባባሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። አንድ የወልዲያ ከተማ ነዋሪ ከወልዲያ በቆቦ አቅጣጫ በኩል ተኩስ እንደሚሰማ ጠቁመው ስጋት ያለባቸው ሰዎች ከተማዋን እየለቀቁ ነው፣ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ትናንት ከግቢ ወጥተዋል ብለዋል። ስለጉዳዩ ተጨማሪ አስተያያት ለማግኘት ለወልዲያን ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንትና ለዩኒቨርሲቲው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ብደውልም ስልክ አያነሱም፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዝግ ነው።

ሌላው ተፈናቅለው ወልዲያ የሚገኙ አስተያየት ሰጪም በቆቦ ከተማ ዝርፊያ መቀጠሉን፤ ነዋሪዎችም በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ወደ ወልዲያ እየገቡ እንደሆነ አስረድተዋል። “የህወሓት ኃይሎች ከቆቦ ወጥተዋል” እየተባለ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚነገረው ሀሰት እንደሆነ አንድ ተፈናቃይ ገልጠዋል። ሌላው ተፈናቃይም «ቆቦ ተለቅቃለች» የሚባለው ወሬ ያልተጨበጠና ያልተረጋገጠ እንደሆነ ነው ለዶቼ ቬሌ ያስረዱት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የቆቦን ከተማ ለቅቆ መውጣቱን መንግሥት ከቀናት በፊት መግለፁ ይታወሳል። አጠቃላይ በግንባሩ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ከመንግሥት ወገን ለማግጣራት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW