በበርሊን የጀርመን አይሁድ ጋዜጣ መታተም መጀመሩ፣
ዓርብ፣ ጥር 4 2004ማስታወቂያ
በጀርመን ሀገር የሚኖሩ፤ ሩሲያውያን፤ ሰርቢያውያን ፣ ፖርቱጋላውያን እስፓኛውያን እንዲሁም ጣልያኖች ሁሉም በየቋንቋቸው የሚታተሙ ጋዜጦች አሏቸው። በተለይ በጀርመን ሀገር ከሚኖሩት የውጭ ዜጎች መካከል በቁጥር ላቅ ያሉት ቱርካውያን ቢያንስ 7 ጋዜጦች ለህትመት ያቀርባሉ። በዚህ ላይ በእንግሊዝኛና በፈረንሳይኛ ም የሚቀርቡ አያሌ ጋዜጦችና መጽሔቶች ለፈላጊዎች በሰፊው ይቀርባሉ። ከሰሞኑ ደግሞ እንደዘገበልን፤ «ጂዊሽ ቮይስ» የአይሁድ ድምፅ ፤ የተሰኘ ጋዜጣ መታተም መጀመሩን ከበርሊን ፣ ይልማ ኃ/ሚካኤል የላከልን ዘገባ ያስረዳል።