1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በባለስልጣናት የቃላት ምልልስ የቀጠለው የኢትዮ ሶማሊያ ዲፕሎማሲ ውጥረት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2016

የኢትዮጵያ የባሕር በር መሻት እና የወሰደችው እርምጃ ያስከተለው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ግንኙነት ውዝግብ አሁንም በሀገራቱ ባለስልጣናት የቃላት ምልልስ ቀጥሏል። በሌላ በኩል የሶማሊያ ሲቪል አቪየሽን ከሀገሪቱ ሉዓላዊነት ጋር በማያያዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ግዛቱ እንዳይበር ሊያግድ እንደሚችል ሰሞኑን አስጠንቅቋል።

Äthiopien Addis Abeba | Treffen AU | Somalia Präsident  Hassan Sheikh Mohamud
ምስል REUTERS

የኢትዮ ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ወዴት ያመራ ይሆን ?

This browser does not support the audio element.

ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ግንኙነት

የኢትዮጵያ የባሕር በር መሻት እና የወሰደችው እርምጃ ያስከተለው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ግንኙነት ውዝግብ አሁንም በሀገራቱ ባለስልጣናት የቃላት ምልልስ ቀጥሏል።

በሌላ በኩል የሶማሊያ ሲቪል አቪየሽን ከሀገሪቱ ሉዓላዊነት ጋር በማያያዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ግዛቱ እንዳይበር ሊያግድ እንደሚችል ሰሞኑን አስጠንቅቋል።

ቱርክ አንካራ ውስጥ መስከረም 7 ይቀጥላል የተባለው የሁለቱ ሀገራት ቀጥተኛ ያልሆነ ሦስተኛ ዙር ንግግር እንዴት ይቋጭ ይሆን? የሁለቱ ጎረቤታም ሀገራት ግንኙነትስ ወደምን ያመራ ይሆን? 

የኢትዮ-ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ትኩሳት ወዴት ?

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስለ ሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የተናገሩት

የኢትዮጵያ የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የሶማሊያ መንግሥት አመራሮች የኢትዮጵያና የሶማሊያ ሕዝቦችን ግንኙነት ከሚያሻክሩ እና የቀጣናውን ሕዝቦች ዘላቂ ጥቅም ከሚፃረሩ አካሄዶች እንዲቆጠቡ ሰሞኑን ጠይቀዋል።

አቶ አደም ይህንን ያሉት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ሁለቱ ሀገራት በቱርክ ካደረጉት ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግራቸው ማግስት ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እስክታከብር ድረስ ሀገራቸው ስለ ንግድም ሆነ ሌሎች ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ጋር እንደማትነጋገር መግለፃቸውን ተከትሎ ነው።

ለሦስተኛ ዙር ቀጠሮ የተያዘለት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት በቱርክ

አቶ አደም ፋራህ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት የሚያበረክተውን አዎንታዊ ሚና አጠናክሮ ለመቀጠል ዝግጁ መሆኑን አመልክተዋል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሰሞኑን ሶማሊያ ስለሚገኘው እና አትሚስ በሚባለው ጥምር ሰለም አስከባሪ ጦር ውስጥ 

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ሶማሊያ ውስጥ በከፈለው የሕይወት፣ የአካልና የንብረት መስዋዕትነት የሶማሊያ መንግሥት ለመጠናከር ስለመብቃቱ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ላይ ተመስርተው የሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምላሽ ሰጥተዋል። 

በቱርክ አሸማጋይነት የቀጠለው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት

ለመሆኑ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻከር ዐቢይ መነሻ ኢትዮጵያ ከራስ ገዝ ሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው የባሕር በር ማስገኛ የመግባቢያ ስምምነት ወይስ ሌላም ተጨማሪ ጉዳይ ይኖር ይሆን? ስንል በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩን ዶክተር ሙዐዝ ግደይን ጠይቀናቸዋል።

"ኢትዮጵያን በተለየ ጥርጣሬ የማየት [ከሶማሊያ በኩል] ልምምድ አለ። ይሄ ባለበት ሁኔታ የሶማሊያን ጥቅም ወይም ግዛታዊ አንድነት የሚነኩ ነገሮች ከሶማሊላንድ ጋር ሲፈፀሙ በችግሩ ላይ ሌላ ችግር ፈጥሮበታል።"

መረጋጋት የራቀው የአፍሪቃ ቀንድ ትኩሳቱ ጨምሯል

የሶማሊያ ምላሽ እና የቀጣይ የሀገራቱ ግንኙነት መልክ

 

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ንግግር ተከትሎ ምላሽ የሰጡት የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ ሞአሊም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ወታደሮች ሱማሊያ ውስጥ ሰላም በማስከበር ዋጋ መክፈላቸውን የሚናገሩት ጉዳይ የሶማሊያን ሉዓላዊነት ለመጣስ ምክንያት ሊሆን እንደማይገባ ተናግረዋል። ለመሆኑ የሁለቱ ሀገራት ባለስልጣናትን ምልልስ ውስጥ ያስገባው የአፍሪካ ቀንድ ሀገራቱ ግንኙነት ወዴት ያመራ ይሆን ? ዶክተር ሙዐዝ ግደይ።

"ኢትዮጵያ በአቋሟ እቀጥላለሁ ካለች ወደ 'ሚሊተሪ ኮንፍሮንቴሽን' ሊሄድ ይችላል፣ ስላማዊ ሂደቱ በሰጥቶ መቀበል የሚመራ ከሆነ ደግሞ ያለው አቋራጭ የመግባቢይ ስምምነቱን አቋርጠህ [ከሶማሊላንድ ጋር የተፈረመውን] ሌሎች አማራጮችን መፈለግና የኢትዮጵያንም የሶማሊያንም ጥቅም ማክበር የሚቻልበትን መንገድ መፈለግ ነው።" 

የቀጠለዉ የኢትዮጵያ እና ሶማልያ ዉዝግብ

 

የሶማሊያ ሲቪል አቪየሽን ያወጣው ማስጠንቀቂያ

በሌላ በኩል የሶማሊያ ሲቪል አቪየሽን ከሀገሪቱ ሉዓላዊነት መከበር ጉዳይ ጋር በማያያዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ግዛቱ እንዳይበሩ ሊያግድ እንደሚችል በዚሁ ሳምንት አስጠንቅቋል።

በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ እየተሰራጨ ያለው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የተላከ የተባለው ደብዳቤ፣ በጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የደብዳቤ ልውውጦች እንደነበሩ ይጠቅሳል፤ ምንም እንኳን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር ባይኖርም። 

ኢትዮጵያ ወታደሮቿ ድንበር አቋርጠዋል የሚለውን የሶማሊያን ውንጀላ አስተባበለች

ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ የገቡበትን ውዝግብ ለመፍታት ቱርክ አንካራ ውስጥ ያደረጉት ሁለተኛው ዙር ንግግር ተጨባጭ መፍትሔ ሳይገኝበት ሲቋጭ ተጠያቂዎቹ ሁለቱ ሀገራት መሆናቸውን ከዚህ በፊት ያነጋገርናቸው የአለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ተንታኝ ተናግረው ነበር።

ውዝግብ ውስጥ የገቡት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የማሸማገል ሚናውን በወሰደችው ቱርክ ተደግፈው ለመስከረም 7 በያዙት ቀጠሮ ዘላቂ ስምምነት ላይ ለመድረስ ይበቁ ይሆን ?

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW