1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በባሕር ዳር የተካሔደው ጣና ፎረም ተጠናቀቀ

እሑድ፣ ጥቅምት 6 2015

በአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ዙሪያ ለሶስት ቀናት ሲመክር የቆየው የጣና ፎረም ውይይት ዛሬ ተጠናቅቋል፣ የዘንድሮው የፎረሙ ውይይት ከሌሎች ጊዜዎች አንፃር ሲታይ የተቀዛቀዘ እንደነበር ተነግሯል፣ በማጠቃለያ ውይይቱ የተገኙት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ ያለው ጦርነት እንዲቆም አሜሪካ ትሰራለች ብለዋል፡፡

Äthiopien Bahir Dar | Tana Forum
ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

በባሕር ዳር የተካሔደው ጣና ፎረም ተጠናቀቀ

This browser does not support the audio element.

በአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ዙሪያ ለሶስት ቀናት ሲመክር የቆየው የጣና ፎረም ውይይት ዛሬ ተጠናቅቋል፣ የዘንድሮው የፎረሙ ውይይት ከሌሎች ጊዜዎች አንፃር ሲታይ የተቀዛቀዘ እንደነበር ተነግሯል፣ በማጠቃለያ ውይይቱ የተገኙት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር  በኢትዮጵያ ያለው ጦርነት እንዲቆም አሜሪካ ትሰራለች ብለዋል፡፡
በየአምቱ የአፍሪካን አህጉር የሰላምና የደህንነት ጉዳይ  በባሕርዳር የሚመክረው የጣና ፎረም ለሶስት ቀናት ሲኬሄድ ሰንብቶ ዛሬ ብዙም ተሰታፊዎች ባልተገኙበት ከሰኣት በኋላ ተጠናቅቋል፡፡ በሰላምና ደህንነት ዙሪያ ለተሳታፊዎች ማብራሪያ የሰጡት የቀድሞው የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጣና ፎረም የቦርድ አባል አቶ ኃይለማሪም ደሳለኝ የዘንድረውን የፎረሙን ይዘት ካለፉት ጋር በማነፃፀር ተችተውታል፡፡
“በአፍሪካ የዳበረ የውይይት ልምድ ጎድላል፣ በእኔ እይታ በዘንድሮው የታና ፎረም ላይ ገና ብዙ የሚቀረን ነገር አይቻለሁ፣ ባለፉት 9 የጣና ፎረም ውይይቶች ብዙ ጉዳዮችን በጥልቀት አይተናል፣ በአሁኑ ስብሰባ ውይይቶች በጥልቀት አልታዩም፣ ጽሁፍ አቅራቢዎች ውይይት ሳይደረግ ከአዳራሽ ሲወጡ አይተናል ይህ ትንሽ ያሳፍራል” ብለዋል አቶ ኃይለማሪም፡፡
አቶ ኃለማሪያም አፍሪካውያን “በአካል ከቅኝ ግዛት የወጣን ብንሆንም የህሊና ቅኝ ተገዥዎች ሆነናል ከዚህ መውጣት ይገባል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡ 
“የአስተሳሰብ ስሪታችን መፈተሸ አለበት አፍሪካውያን የራሳችንን ደህንነትና ሰላም ማስጠበቅ አለብን፣ ከአካል ቅኝ ተገዥነት ወጥተን ይሆናል ከህሊና ቅኝ ተገዥነት ግና ገና አልወታንም፣ አዕምሯችንን ነፃ ልናወጣው ገባል፣ ወደ ውስጣችን ማሰብ ይገባል፣ ስላለፈው መቆዘምኤገባም፣ በዚህ ፎረም ማለት የምፈልገው ይህንን ነው፡፡”
አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው መፍታት የሚችሉት የውጪ ጫናን መቀነስና መቋቀቋም መሆኑን የጠቀሱት አቶ ኃይለማሪም፣ አፍሪካ ህብረት አሁን 75 ከመቶ የሚሆነውን በጀቱን ከውጪ አገራት እንደሚያገኝ አመልክተዋል፣ ታዲያ በድጎማ በአፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ማስፈን ይቻላል ውይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በስነስርኣቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ደግሞ አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው መፍታት ይኖርባቸዋል ብለዋል፤ አሜሪካም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደምታደርግ አስረድተዋል፡፡
በኢትዪጵያ ያለው ጦርነት እንዲቆምና ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከጦርነትና ከሰቆቃ እንዲወጡም አገራቸው ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ አብራርተዋል፡፡
“አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ለመስራት ዝግጁ ናት፣ የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፈታት አለበት የሚለውን እሳቤም ትደግፋለች፡፡ አሜሪካ የኢትዮጵያ አንድነት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር ትሻለች፣ይህ የአሜሪካ ፖሊሲ ነው፣በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ዋሽንግተን ከልብ ትሰራለች ሁሉም ለኢትዮጵያውያን ብልፅግናና ሰላም እንዲመጣ አሜሪካ ሁሌም ዝግጁ ናት” ብለዋል፡፡
ፎረሙ ዛሬ ከሰዓት ተጠናቀቀ ሲሆን የፎረሙን ሂደት ብዙም ተሳትፎ የሌለበትና የተቀዛቀዘ ነበር፡፡
አለምነው መኮነን
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW