1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለአግባብ ዋጋ ጨምረዋል የተባሉ የንግድ ተቋማት ተቀጡ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 9 2016

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ1ሺ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮ ትናንት በማህበራዊ መገናኛ ዜዴ እንደገለጸው እርምጃው የተወሰደው ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸውና ምርት በመደበቃቸው ነው፡፡

Äthiopien | Straßenszene in Assosa
ምስል Negasa Desalegn/DW

በአሶሳ ከተማ በህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል

This browser does not support the audio element.

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለአግባብ ዋጋ ጨምረዋል የተባሉ የንግድ ተቋማት ተቀጡ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ1ሺ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮ ትናንት በማህበራዊ መገናኛ ዜዴ እንደገለጸው እርምጃው የተወሰደው ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸውና ምርት በመደበቃቸው ነው፡፡ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ዋጋ የሚጨምሩ እና ምርት የሚደብቁ አካላትን ለመቆጣጠር በክልል ደረጃ የተቋቋመው ግብር ሐይል ወደ ስራ መግባቱን ጠቁመዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ቢሮው በመሄድና በስልክ የስራ ኃላፊዎችን ለማናገር ያደረኩት ተደጋጋሚ ጥረት ስብሰባና ስምሪት ላይ ነን በማለታቸው አልተሳካም፡፡ በአሶሳ ከተማ ከባለፈው ሳምንት ረቡዕ ነሔሰ 1 ጀምሮ በተለያዩ ፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪዎች መታየታቸውን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲከፈቱ መፈቀዱ

ምርት በመደበቅና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ በክልሉ የተለያዮ አካባቢዎች እርምጃ መውዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ንግድና የገበያ ልማት ቢሮ አመልክቷል፡፡ በአሶሳ፣ መተከልና ካማሺ ዞን ውስጥ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪዎች ተስተውሏል፡፡

ምርት በመደበቅና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ በክልሉ የተለያዮ አካባቢዎች እርምጃ መውዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ንግድና የገበያ ልማት ቢሮ አመልክቷል፡፡ በአሶሳ፣ መተከልና ካማሺ ዞን ውስጥ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪዎች ተስተውሏል፡ምስል Negassa Dessalegen/DW

በአሶሳ ከተማ የተስተዋለው የዋጋ ጭማሪ

በአሶሳ ከተማ ከባለፈው ሳምንት ረቡዕ አንስቶ የመሰረታዊ ፍጆታና የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ መጨመሩ ተገልጸዋል፡፡ በአሶሳ ከተማ ውስጥ በትናትናው ዕለትም በነበረው የገበያ ውሎ በተወሰኑ የፍጆታ ምርቶች ላይ ከ150 አስከ ከ300 ብር ጭማሪዎች መታየታቸውን ያነጋርናቸው ነዋሪዎች አስታውቋል፡፡ የፍጆታ ምርቶችን ዋጋ በዝርዝር ነዋሪዎቹ  ገልጸዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና አንደምታዎች

በሀገሪቱ የተጀመረውን የኢኮኖሚ ሪፎርም  ምክንያት በማድረግ ያለአግባብ ዋጋ የጨመሩ ግለሰቦችን ለመቆጣጠር በዚሁ ወር መጀመሪያ ወደ ስራ መግባቱ የተነገረው የተለያዩ ተቋማት የተሳተፉበት ግብረ ሀይል በክልል ደረጃ በሁሉም አካባቢዎች ያለአግባብ ዋጋ የጨመሩ የንግድ ተቋማትን ማሸጉንና ሌሎች እርምጃዎችን መውሰዱን ገልጸዋል፡፡

በአሶሳ ከተማ በህገ ወጦች ላይ የተወሰደ እርምጃ 

በአሶሳ ከተማ ውስጥ በርካታ ንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን በገበያ ማዕከልና ሱቆች ባደረኩት ምልከታ ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ ሆኖም በከተማው የፍጆታ ምርቶች ዋጋ ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር የዋጋ መቀነስ አለማሳየቱን ሸማቾች ይናገራሉ፡፡ ከፍጆታ ምርቶች በተጨማሪ እንደ ሲምንቶ ያሉት የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ መጨመሩን፤ እንደዚሁም ከገበያ እየጠፋ መሆኑንና ጥቂት ቦታዎች ብቻ እንደሚገኝ ከነዋሪዎቹ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በከተማው የፍጆታ ምርቶች ዋጋ ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር የዋጋ መቀነስ አለማሳየቱን ሸማቾች ይናገራሉ፡፡ ምስል Negassa Dessalegen/DW

በኢትዮጵያ ያለው ግጭት፤ የኢኮኖሚ ማሻሻያው አተገባበር ስጋት

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንደ አሶሳ ከተማ፣ ግልገልበስ ከተማ፣ፓዌ ወረዳ፣ቡሌን እና ሌሎችም አካባቢዎች ያለአግባብ ዋጋ ጭማሪ አድርጓል የተባሉ የንግድ ተቋማት መቀጣታቸውን የክልሉ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡

ዋጋ ለማረጋጋት ጤፍና የተለያዩ ምርቶችን ከሌሎች አካባቢዎች በማስመጣት በተተመነ ዋጋ ለህብረተሰቡ በመሸጥ ላይ እንደሚገኝ ተገልጸዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የሚመረቱና የውጪ ምንዛሪ የማይጠይቁ ምርቶች ዋጋ በከተማው መጨመሩን ባለፈው ሳምንት ረቡዕ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW