በቤንሻንጉል ያላባራው የሰላማዊ ዜጎች ጥቃት
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 5 2013
ማስታወቂያ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከልን ዞን ቡለንና ድባጢ ወረዳ ነዋሪዎች ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱባቸው መሆኑን አመለከቱ። በክልሉ የመተከል ዞን የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር /ኮማንድ ፖስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ በበኩሉ ከ1000 የሚበልጡ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩቸው እየታየ እንደሚገኝ ትናንት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም በየደረጃው ያሉ አመራሮችን እና የፖሊስ አባላት ላይ ጭምር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ባላቸው ላይ እርምጃ መውሰዱን አመልክቷል። ሕግን ለማስከበር በሚያደርገው ጥረትም 277 ዘመናዊና ባህላዊ የጦር መሣሪያዎችን እንዲሁም የወታደር አልባሳቶችንም በቁጥጥር ስር ማዋሉን ጠቁሟል። ከባለፈው ረቡዕ አንስቶ በቡለን ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች ውስጥ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አምስት የሚደርሱ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል። በተለያዩ ጊዜያ ታጣቂዎች በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ሸዋዬ ለገሠ
እሸቴ በቀለ