1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ላይ የባለሙያዎች አስተያየት

ሰለሞን ሙጬ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 7 2017

ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የሚገዙበት እና የሚሸጡበት የዋጋ ልዩነት ከ2 በመቶ እንዳይበልጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰሞኑን ያወጣው አዲስ መመሪያ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።በዚህም የንግድ በንኮች የውጭ ምንዛሪ የሚገዙበትን ዋጋ ከፍ እያደረጉ የሚሸጡበትን ደግሞ እየቀነሱ መሆኑ ተስተውሏል።

Thumbnail Business Beyond | Can anything challenge the almighty dollar's dominance
ምስል Karel Navarro/AP Photo/picture alliance

በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ላይ የባለሙያዎች አስተያየት

This browser does not support the audio element.

 

ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የሚገዙበትእና የሚሸጡበት የዋጋ ልዩነት ከ2 በመቶ እንዳይበልጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰሞኑን ያወጣው አዲስ መመሪያ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።በዚህም የንግድ በንኮች የውጭ ምንዛሪ የሚገዙበትን ዋጋ ከፍ እያደረጉ የሚሸጡበትን ደግሞ እየቀነሱ መሆኑ ተስተውሏል።
 

ብሔራዊ ቤንክ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው በሌሎች ሀገሮች ያለውን ተጨባጭ እውነታ እና አሠራር ተንተርሶ መሆኑን ገልጿል።በዚህ ጉዳይ ላይ ሦስት የገንዘብ አስተዳደር እና የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎችን አስተያየት ጠይቀናል ።

"መግዣ እና መሸጫ ዋጋ ስናይ የትም ዓለም ትንሽ ልዩነት ነው ያለው። የገንዘቡን ውጣ ውረድ እሱን ለመቆጣጠር ብሎ ነው [መንግሥት] እና.... አንደኛው ሸማቹን ለመከላከል ነው። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ባንኮቹ ራሳቸው የጥቁር ገበያ ሥርዓት ውስጥ እንዳይገቡ በሚል ይመስለኛል"። ይህ እርምጃ የተወሰደው ብለዋል - ዶክተር ቄስጠንጢኖስ በርኸ ተስፋ።
"የኢትዮጵያ መንግሥት በሁለት የፖሊሲ አጣብቂኝ ውስጥ ያለ ይመስላል። አንድ ጊዜ ነፃ ገበያ አድርገህ ሌላ ጊዜ ደግሞ የብር ዝውውርን በአንድ በኩል ገድበህ በዚያ መካከል የነፃ ገበያ ምህዳራዊ ሁኔታውን እንዴት እንደሚያስኬድ ግራ የሚገባ ነው። ሁለተኛ በነፃ ገበያ ይወሰን ነው የተባለው የውጭ ምንዛሪ ሁኔታው ግን አሁን ደግሞ ብሔራዊ ባንክ ጣልቃ ገብቶ የዋጋ ተመን አስቀምጧል። ይህ ከመጀመርያው ከተነገረን ምክረ ሀሳብ አንፃር እርስ በርሱ የሚጣረስ ነው።..... ቁጥጥር ነው በተዘዋዋሪ"። የፋይናንስና የኢኮኖሚ አማካሪና መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ዳዊት ታደሰ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ ባወጣዉ መመሪያ መሠረት የዉጪ ገንዘብ መግጪያና መጪያ ዋጋ ልዩነት ከሁለት በመቶ መብለጥ የለበትምምስል Solomon Muche/DW

"መንግሥት ጣልቃ በመግባቱ መቃወሜ አይደለም። ግን መርሁ ስለተጣረሰብኝ ነው። በእርግጥ ጣልቃ መግባቱ - መንግሥት ለሕብረተሰቡ ጠቀሜታ ሊኖረው እንደሚችል ነው የሚታሰበው። ለሸማቹ የዋጋ ፋታ ለማግኘት ዕድል እንደሚሰጠው ነው የሚታየኝ"። ሽዋፈራሁ ሽታሁን የፖለቲካ ኢኮኖሚ ተንታኝ
 
የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን ገበያ መር በሆነ መንገድ መተመናቸውን ይቀጥላሉ ይላል። 

ሰለሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW