1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጉብኝቱ አላማ ስለድርቁ ለለጋሽ አካላት ለማስገንዘብ ነው

ሐሙስ፣ ሰኔ 1 2009

ከዛሬ ጀምሮ ለስድስት ቀናት የሚቆየው የልዑካኑ ጉብኝት ድርቅ ያጠቃቸውን ሶማሊያን እና ኬንያንም ያጠቃልላል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሰብዓዊ ጉዳዮች መልዕክተኛ አህመድ አልማራኪ እና የመካከለኛው ምሥራቅና የማዕከላዊ እስያ ሃገራት አጋርነት ተልዕኮ ኃላፊ ረሺድ ሃኒኮፍ የልዑኩ አካል ናቸው፡፡

Äthiopien Gode - Dürre-Krise
ምስል DW/J. Jeffrey

«ጠ/ሚ ዐብይ ዬኤስ አሜሪካን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል»

This browser does not support the audio element.

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባባሪያ ጽህፈት ቤት (OCHA) እና የአፍሪካ ኅብረት በጥምረት ያዘጋጁት የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት የከፍተኛ ልዑካን ጉብኝት ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ ለስድስት ቀናት የሚቆየው የልዑካኑ ጉብኝት ኢትዮጵያን ጨምሮ ድርቅ ያጠቃቸውን ሶማሊያን እና ኬንያን ያጠቃልላል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሰብዓዊ ጉዳዮች መልዕክተኛ አህመድ አልማራኪ እና የመካከለኛው ምሥራቅና የማዕከላዊ እስያ ሃገራት አጋርነት ተልዕኮ ኃላፊ ረሺድ ሃኒኮፍ የልዑኩ አካል ናቸው፡፡ የአፍሪካ ኮሚሽን፣ የዩናይትድ ስቴትስ፣ የሳዑዲ አረቢያ፣ የኳታር እና የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት በጉብኝቱ ይሳተፋሉ፡፡ የጉብኝቱ አላማ ያለውን ሁኔታ ለለጋሽ አካላት ለማስገንዘብ መሆኑን የOCHA ረዳት ቃል አቃባይ ለዶይቸ ቨለ ገልጸዋል፡፡ የዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን ያጠናቀረውን ዘገባ የድምጽ መስፈንጠሪያውን ተጭነው ያድምጡ፡፡    

 

መክበብ ሸዋ

ተስፋለም ወልደየስ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW