በተ.ዐ.ኤሚሬትስ ያሉ የኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች እጣ ፈንታ
ሐሙስ፣ መስከረም 17 2011ማስታወቂያ
የምህረት አዋጁ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል የሆኑት ወደ ሀገር መግባት የሚፈልጉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን እድሉን በመጠቀም ያለ ምንም ቅጣት ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ግን ከፓስፖርት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ችግር የተለያዩ መሰናክሎች እየገጠማቸው መሆኑን ይናገራሉ። ፓስፖርታቸው ያልታደሰ ፤ የጠፋባቸው አዲስ ፓስፖር ማውጣት የጀመሩ ፤ ፓስፖርታቸው በአሰሪዎቻቸውና በኢምሬት ኢምግሬሽን በኢንባሳቸው በኩል የተላከላቸው ዜጎች በአሰራር መጓተትና ወደ ሀገር ቤት የተላከው ፓስፖርት በፍጥነት ስለማይደርስላቸው መቸገራቸውን ስልክ በመደወል ያነጋገርኳቸው ማንነታቸው እንዳይነገር የፈለጉ የዱባይ ነዋሪዎች ገልጸውልኛል ። ኢትዮጵያውያን ዙሪያ ስለሚታየው የፓስፖርት አቅርቦትና በሰነድ አለመሟላት ችግር የአረብ መገናኛ ብዙሃና ትኩረት የሳበ መሆኑ ይጠቀሳል።
ነቢዩ ሲራክ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ