1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቱርካይ ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር ከ3,400 በላይ ደረሰ

ማክሰኞ፣ ጥር 30 2015

እስካሁን 3,419 ዜጎቻችን አጥተናል። 20,534 ደግሞ ተጎድተዋል። ከ8 ሺሕ ዜጎች በላይ ከሕንጻዎች ፍርስራሽ ሥር አውጥተናል። 5,775 ሕንጻዎች ተደርምሰዋል።

Türkei Osmaniye Erdbeben Trauer
ምስል Khalil Hamra/AP Photo/dpa

በቱርካይ ባጋጠመ ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር ከ3,400 በላይ ደርሷል።

This browser does not support the audio element.

በቱርካይ ሶርያ ድንበር በተከሰተው ርዕደ መሬት ከ5 ሺሕ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ታውቋል። በፍርስራሾች የተደፈኑ ሰዎች በሕይወት የማትረፍ ስራው ተጠናክሮ ቢቀጥልም ተስፋው ግን እየተመናመነ እንደሆነ ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ዝርዝሩን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር አጠናቅሮታል።

በቱርካይ እና ሶርያ ድንበር በ12 ሰዓታት ልዩነት ለሁለተኛ ጊዜ በተከሰተው ርዕደ መሬት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከ5ሺሕ በላይ ዜጎችን ሕይወት ቀጥፏል። በቱርክ 3,400 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ሲረጋገጥ፤ ከ20 ሺሕ በላይ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሃገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ባለስልጣን አስታውቋል።

በሶሪያ ባጋጠመው ተመሳሳይ አደጋ ደግሞ ቢያንስ 1,622 ሰዎች ሲሞቱ 3,649 መጎዳታቸውን የሃገሪቱ ባለስላጣናት አስታውቀዋል።

ምስል Omar Haj Kadour/AFP

በቱርካይ ባጋጠመ ርዕደ መሩት ቤተሰቦቹ በፍርስራሽ እስካሁን ተደፍነው በሕይወት ከወጡለቸው እየተጠባበቁ ያሉት አባት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ

``` በፍርስራሹ ሥር 4 ሰዎች አሉ። እህቴ፣ ባለቤቷ፣ አንድ ወንድ ልጇና አንድ ሴት ልጇ ከትላንት ረፋድ 4 ሰዓት ጀምሮ እስካሁን በፍርስራሽ እንደተቀበሩ ነው።``

 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በሕይወት የተረፉትን ለማፈላለግ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ተስፋቸው እንደተሟጠጠ እየተነገረ ነው። አንድ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ተከታዩን ብሏል።

`` በቱርክና በሶርያ የሚገኙ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች ፍርስራሹ ውስጥ እንደተቀበሩ ስለሚታመን የሟቾቹ ቁጥር በፍጥነት ተለዋውጧል ።``

የተለያዩ የዓለም ሃገራት በአደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ከመግለጽ ባሻገር የሕይወት አድን ስራውን እየተቀላቀሉ ነው። የአውሮፓ ሕብረት ዛሬ ባካሄደው ኮንፈረንስ ሟቾቹን የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት በማድረግ አስቧል። በተለያዩ የዓለም ሃገራት በሚገኙ የቱርካይ ኤምባሲዎችም ዜጎች ሐዘናቸውን እየገለጹ ነው።

የቱርክ ምክትል ፕረዚደንት ፉአት ኦክታይ የሟቾች ቁጥር 3,419 መድረሱን ይፋ አድርገዋል።

`` እስካሁን 3,419 ዜጎቻችን አጥተናል። 20,534 ደግሞ ተጎድተዋል። ከ8 ሺሕ ዜጎች በላይ ከሕንጻዎች ፍርስራሽ ሥር አውጥተናል። 5,775 ሕንጻዎች ተደርምሰዋል። ከዋናው ርዕደት በተጨማሪ 312 መናወጦችም ተመዝግቧል።``

በቱርካይ እና ሶርያ ድንበር ያጋጠሙ ርዕደ መሬቶች  በሬክተር የርዕደ መሬት መለኪያ 78 እና 75 የተለኩ መሆናቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የጂኦሎጂያዊ ጥናት ተቋም አስታውቋል። የዜና ምንጮቻችን የጀርመን የዜና አገልግሎት DPA እና አሰሽየትድ ፕረስ ናቸው።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

እሸቴ በቀለ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW