1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በታጣቂዎች እገታ ስር የነበሩ 3 የኦሮምያ ክልል አቃቤያነ ሕግ መለቀቃቸው

ሰኞ፣ ኅዳር 29 2018

በኦሮምያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ እገታ ስር ከነበሩ 3 የኦሮምያ ክልል አቃቢያነ ሕግ ባለፈው ቅዳሜ መለቀቃቸውን የኦሮምያ ክልል የአቃቤያነ ሕግ ማኅበር ዛሬ አስታወቀ ። እገታው በተፈጸመበት ወቅት ከተያዙት መካከል አንዱ መገደላቸውን ዶቼቬለ ከዚህ ቀደም ዘግቧል።

Äthiopien West Shoa 2025 | Oromia-Religion zum Neujahr
ምስል፦ Seyoum Getu/DW

በታጣቂዎች እገታ ስር የነበሩ 3 የኦሮምያ ክልል አቃቤያነ ሕግ መለቀቃቸው

This browser does not support the audio element.

 

በኦሮምያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞንውስጥ እገታ ስር ከነበሩ 3 የኦሮምያ ክልል አቃቢያነ ሕግ ባለፈው ቅዳሜ መለቀቃቸውን የኦሮምያ ክልልየአቃቤያነ ሕግ ማኅበር ዛሬ አስታወቀ ። እገታው በተፈጸመበት ወቅት ከተያዙት መካከል አንዱ መገደላቸውን ከዚህ ቀደም ተዘግቧል። ቀሪዎቹም በአጋቾች እጅ እንደነበሩም በወቅቱ ተገልጿ ነበር። ከታጋቾቹ አንዱ ፅኑ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ናቸው ።

ለመሆኑ ታጋቾቹ እንዴት ተለቀቁ? ሂደቱስ እንዴት ነበር እገታውን የተመለከቱ መረጃዎቹን ሲከታተል ከነበረው ባልደረባችን ታምራት ዲንሳ ጋር ስለ አቃቤ ሕጉ ግድያና የሌሎቹ አቃቤያነ ሕግ እገታ መቼና የት እንዴት እንደተካሄደ ሂደቱም እንዴት እንደነበረ እንዴት እደተለቀቁ አጭር ቃለ ምልልስ አድርገናል። 


ታምራት ዲንሳ 
ኂሩትመለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW