1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

በትራምፕ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራና ፖለቲካዊ አንደምታው

እሑድ፣ ሐምሌ 7 2016

ነገ የሚጀመረውና የሪፐብሊካን ፓርቲ ዶናልድ ትራምፕን እጩው አድርጎ በይፋ የሚመርጥበት የሪፐብሊካኑ ጉባኤም የዚሁ የግድያ ሙከራ ተጸዕኖ ገፈት ቀማሽ ነው። ለወትሮውም ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበትና፣ ሚልዋኪ፣ ዊስኮንሰን ውስጥ በሚደረገው በዚሁ ጉባኤ ላይ ዶናልድ ትራምፕ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

USA Butler Wahlkampf Trump Zwischenfall
ምስል Evan Vucci/AP Photos/picture alliance

የትራምፕ የግድያ ሙከራና ፖለቲካዊ አንደምታው

This browser does not support the audio element.

ፕሬዝዳንታዊ ተፎካካሪና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተሞከረው የግድያ ሙከራ ከሁለቱም የፖለቲካ ጎራወች ያስገኘው ምላሽ አንድ ነው። ሁሉም ባንድ ቃል ሙከራውን ኮንነዋል። በሃገሪቱ ውስጥ እየተባባሰ ያለውን የፖለቲካ ውጥረት እንዲሁም አመጽንና ግድያን ሊጋብዝ የሚችል ልክ አልባ ዕሰጣገባ ሊቆም ይገባዋል ብለዋል።

የአሜሪካኑ የፕሬዝዳንቶች ጥበቃ ቡድን ጥበቃውን የበለጠ እንዲያጠናክር ማሳሰቢያ የሰጡም አልጠፉም። ከዚህ አለፍ ብለውም አጋጣሚውን በአሜሪካ የፖለቲካ ክርክር ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘውን የጦር መሳርያ ቁጥጥር ማጠናከር አስፈላጊነት ለመጠቆም የተጠቀሙበትም አልጠፉም። ብቻ ከህዝቡ ምላሽ፣ ከመገናኛ ብዙሃን ሽፋንም ሆነ ከሁለቱም ፓርቲ መሪወች የተሰማው ሃገሪቷ እያመራች ያለችው ወደ ግጭትና አመጽ ነውና መስመራችን ይስተካከል የሚል ነው።

ይሄው የግድያ ሙከራ ወትሮውንም ውጥረት የበዛበትን የአሜሪካ ፖለቲካ የበለጠ ሊያከረው ይችላል የሚል ስጋትም አለ። ሌላው ይሄንኑ ክስተት ተከትሎ የሚመጣው የተጠናከረ የደህንነት ጥበቃ አስፈላጊነት ነው። በአሜሪካ የውጪ ግንኙነት፣ በአለም አቀፍ ገበያው፣ አሜሪካ በምትከተለው ሁለንተናዊ ፖሊሲና በዲሞክራሲያዊ መዋቅሮቿ ላይም ይሄው ክስተት ጥላውን ማጥላቱ አይቀሬ ነው።  

ነገ የሚጀመረውና የሪፐብሊካን ፓርቲ ዶናልድ ትራምፕን እጩው አድርጎ በይፋ የሚመርጥበት የሪፐብሊካኑ ጉባኤም የዚሁ የግድያ ሙከራ ተጸዕኖ ገፈት ቀማሽ ነው። ለወትሮውም ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበትና፣ ሚልዋኪ፣ ዊስኮንሰን ውስጥ በሚደረገውበዚሁ ጉባኤ ላይ ዶናልድ ትራምፕ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ዶናልድ ትራምፕ የግድያ ሙከራ ከተፈጸመባቸው በኋላምስል Brendan McDermid/REUTERS

ሙከራው የፓርቲያቸውና የራሳቸው መሰረት የሆነውን ደጋፊያቸውን የበለጠ የሚያጠናክርና የሚያጸና እንደሆነ ይጠበቃል። ዶናልድ ትራምፕ የረብሻና የብጥብጥ መሪ ናቸው የሚለውን እሳቤም ወደ ብጥብጥና ግጭት ሰለባነት የሚቀይር ትርክትን ለመፍጠር መንገድ እንደሚሆናቸው ሙከራውን ተከትሎ ያገኙት ምላሽ አመላካች ነው።

ዶናልድ ትራምፕን የዲሞክራሲ ጸር እና ስጋት አድርገው ያስቀመጡት ጆ ባይደንና የዲሞክራት ፓርቲም ይሄንኑ ዘመቻቸውን ቀዝቀዝ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ልክ ከዚህ ቀደም ተደርገው ዛሬም ድረስ አከራካሪ ሆነው እንደቆዩ ተመሳሳይ ክስተቶች ሁሉ የአሁኑ ሙከራም ከጀርባ የተጠነሰሰ ሴራ ነው የሚል እሳቢ ወይም  ማስከተሉም እየተስተዋለ ነው።

አሜሪካ ከዚህ ቀደም ከተገደሉባት ሁለት ፕሬዝዳንቶች ማለትም ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኪኔዲና አብረሃም ሊንከን ሌላ ሁለቱንም ሩዘቬልቶችና ሮናልድ ሬገንን ጨምሮ በሰባት ፕሬዝዳንቶች ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጓል። ከፕሬዝዳንታዊ እጩ ተፎካካሪወች ደግሞ እኤአ በ1968 ዓ/ም ከተገደሉት የጆን እኢፍ ኬኔዲ ወንድም ሮበርት ኪኔዲ ሌላ ሁለት ፕሬዝዳንታዊ እጩወች የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል። 

አበበ ፈለቀ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW