1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትራምፕ ማሸነፍ የአፍሪካ መሪዎች ተስፋ

ፀሀይ ጫኔ
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 30 2017

የአፍሪካ መሪዎች ተመራጩን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን እንደሌሎቹ የዓለም ሀገራት መሪዎች የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክቶቻቸውን አስተላልፈዋል። ከደስታ መግለጫው ባሻገር አብዛኞቹ በአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ብሩህ ተስፋ ሰንቀዋል።

Kenia Nairobi | Reaktionen auf Präsidentschaftswahl in den USA
ምስል Henry Naminde/AP Photo/picture alliance

በትራምፕ ማሸነፍ የአፍሪካ መሪዎች ተስፋ

This browser does not support the audio element.

የአፍሪካ መሪዎች ተመራጩን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን እንደሌሎቹ የዓለም ሀገራት መሪዎች የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክቶቻቸውን አስተላልፈዋል። ከደስታ መግለጫው ባሻገር አብዛኞቹ በአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት  ብሩህ ተስፋ አላቸው።
የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አገራቸው ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር ለመተባበር ፈቃደኛ መሆኗን ሲገልጹ፣ «ዚምባብዌ ከእርስዎ እና ከአሜሪካ ሕዝብ ጋር የተሻለ፣ የበለፀገ እና የበለጠ ሰላማዊ ዓለም ለመገንባት ለመስራት ዝግጁ ነች።»ብለዋል።

ከአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የኢኮኖሚ መሻሻል ይጠብቃሉ 

በናይጄሪያ የመረጃ እና ስትራቴጂ ልዩ አማካሪ ባዮ ኦናኑጋ በተፈረመ መግለጫ ላይፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒዩ ባስተላለፉት መልዕክት «በጋራ የኢኮኖሚ ትብብርን ማጎልበት፣ ሰላምን ማስፈን እና ለዜጎቻችንን ተግዳሮት የሆኑ አለም አቀፍ ተግዳሮቶችን መፍታት እንችላለን» ብለዋል።
በደቡብ አፍሪካ የሶፋሶንኬ ፓርቲ ብሔራዊ አስተባባሪ ፍሪማን ቤሄንጉ ለDW እንደተናገሩት የትራምፕ ማሸነፍ ያስደሰታቸው ከደቡብ አፍሪካ ጋር በድንበርና በህገ ወጥ ስደት ላይ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ስላላቸው ነው።
.«ልክ እንደእኛ ተመሳሳይ ርዕዮተ ዓለም እና እምነት ባለው ሰው ደስተኞች ነን። ከድንበር አንፃር እና ከሕገወጥ ስደትም  አንፃር  የጀርባ አጥንት ይሆነናል። እዚህ ደቡብ አፍሪካውስጥ የህገ ወጥ ስደትን ጉዳይ ለመታገልም የበለጠ ጥንካሬ ይሰጠናል።»ብለዋል።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሀገራቸው እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የቅርብ አጋርነት እና የጋራ ተጠቃሚነት ለማስቀጠል በጉጉት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል ።

በጆሃንስበርግ ነዋሪ የሆኑት ኤሪክ ማቲውስ በደቡብ አፍሪካ ድህነት በመስፋፋቱ የትራምፕ የአሜሪካ ኢኮኖሚ አስተዳደር በደቡብ አፍሪካ የራንድ ገንዘብ ዋጋ ላይ በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ተስፋ አድርገዋል።
«ታውቃለህ, የተለያዩ ስሜቶች አሉኝ። በሌላ በኩል፣ እንደ ፕሬዚዳንት ስለ ዶላር እና ስለ ራንድ ሁኔታ አንድ ነገር እንደሚያደርጉ ተስፋ እናደርጋለን። ምክንያቱም እዚህ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነገሮች በሚለዋወጡበት ጊዜ ሁሉ ይሰማናል። እውነትም መደረግ ያለበት ነገር ነው። ምክንያቱም እዚህ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ድህነት ተስፋፍቷል ለማለት እችላለሁ። ስለዚህ እዚያ የሚቀየር ከሆነ ምናልባት የምናከብረው ወይም የምንደሰትበት ነገር ይኖረን ይሆናል።»በማለት ገልፀዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትምስል Win McNamee/AFP/Getty Images

አንዳንዶች ትራምፕ  ጦርነቶችን ያስቆማሉ ብለው ያስባሉ

የአሜሪካ ምርጫ ውጤትን ተከትሎ አፍሪካውያን በማህበራዊ መገናና ዘዴዎች ምላሽ ሲሰጡ ቆይተዋል። አንዳንዶቹ ውጤቱ ለአሜሪካ ትልቅ ድል ነው ሲሉ ፤ትራምፕ የአለምን ቀጣይ ጦርነቶች ያቆማሉ ብለው ያስባሉ። ሌሎች ደግሞ ድሉ የመጣው ትራምፕ የተሻለ ተቃዋሚ ስላልነበራቸው እና አሜሪካውያንም  ሀገራቸውን  ሴት እንድትመራ  ዝግጁ ባለመሆናቸው ነው ብለዋል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለትራምፕ ድል ምላሽ ከመስጠታቸው በፊት ከስልጣን የተነሱት  የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ ለትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት በ ኤክስ ገፃቸው ለጥፈዋል።
ለሁለት አመታት ብቻ በምክትል ፕሬዚዳንትነት  የቆዩት ጋቻጓ ወደ ፖለቲካው ለመመለስ እየፈለጉ መሆኑን እና በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ሁለት ጊዜ የተከሰሱት ትራምፕ ማሸነፋቸው ለእርሳቸው የሚያበረታታ ነገር ሊሆን ይችላል ተብሏል።

በትራምፕ አስተዳደር አገዋ እንቅፋት ሊገጥመው ይችላል

ተንታኞች እንደሚሉት ከቀረጥ እና  ከኮታ ነፃ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ምርቶችን  ለመላክ ዕድል የሚሰጠውየአሜሪካ-አፍሪካ የንግድ ስምምነት አጎዋ፣ ቀደም ሲል በነበራቸው የአሜሪካ ሸቀጦች የገበያ ተደራሽነት ፍላጎት፤ በትራምፕ አስተዳደር ከፍተኛ እንቅፋት ሊገጥመው እንደሚችል ተንታኞች ተናግረዋል። 

በኪንሻሳ በመጪው አመት የሚካሄደውን የአጎዋ ፎረም በማዘጋጀት ላይ የሚገኘው የዲሞክራቲክ ኮንጎ የንግድ ሚኒስትር ጁሊያን ፓሉኩ ካሆንጊያ፤ ሀገራቸው በተለይም  ከአጎዋ  ንግድ በተሟላ ሁኔታ ተጠቃሚ እንድትሆን ከትራምፕ አስተዳደር ጋር እንደሚሰሩ ተናግረዋል። .
«በአዲሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉትን የመዋዕለንዋይ ፍሰት እድሎች ለማሳየት ለዚህ ታላቅ መድረክ ስኬታማነት እንሰራለን።  እንዲሁም በበጎ የማይታየውን የሀገሪቱን ገጽታ የበለጠ በማሻሻል፤ ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በቂ መዋዕለንዋይ መሳብ እንችላለን።»ሲሉ ለDW ተናግረዋል።
በዚህ ሁኔታ ከመላው አፍሪቃ  ሌሎች መሪዎችም ለትራምፕ እንኳን ደስ አለዎት በማለት አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በአፍሪካ አህጉር የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

 

ፀሐይ ጫኔ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW