1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራዩ ጦርነት ሱዳን የተሰደዱ ዜጎች ጥሪ

ሐሙስ፣ ሰኔ 27 2016

ሱዳን መጠለያዎች እንደሚገኙት ከ30 ሺህ ገደማ የትግራዩ ጦርነት ተፈናቃዮች ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ራውያን አካባቢ ከልጆቻቸውጋር ይኖሩ የነበሩት እናት ወይዘሮ ጊቱ አለፈ፥ ከሕዳር 2013 ዓም ወዲህ ኑሮአቸው በሱዳን መጠልያ ነው። ሱዳን ወደ እርስ በርስ ግጭት በማምራትዋ በሺዎች የሚቆጠር ስደተኞች ለአደጋ መጋለጣቸውን ያነሳሉ።

የትግራይ ተፈናቃዮች ሰልፍ
የትግራይ ተፈናቃዮች ሰልፍምስል Million Haileslasse/DW

በትግራዩ ጦርነት ሱዳን የተሰደዱ ዜጎች ጥሪ

This browser does not support the audio element.

የትግራዩ ጦርነት ተከትሎ ወደ ሱዳን የተሰደዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሱዳኑ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት አደጋ ላይ መውደቃቸው ገለፁ። እነዚህ 60 ሺህ ገደማ የሚገመቱ እና በሱዳን ተነድባ እና ዑምራኩባ የተባሉ መጠልያዎች ያሉ የትግራይ ጦርነት መቀስቀሱ ተከትሎ ወደ ሱዳን የተሰደዱ ስደተኞች የኢትዮጵያ መንግስት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሱላቸው ይጠይቃሉ።

በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና የትግራይ ሐይሎች መካከል በ2013 ዓመተምህረት ጦርነት ሲቀሰቀስ በአብዛኛው ከሑመራ እና ሌሎች ከሱዳን ጋር ከሚዋሰኑ አካባቢዎች ተፈናቅለው፣ ድንበር ተሻግረው ሱዳን የገቡ ዜጎች የከፋ ሁኔታ ላይ መሆናቸው ይገልፃሉ። ያነጋገርናቸው በሱዳን ዑምራኩባ እና ተነድባ የተባሉ የስደተኞች መጠልያ ጣብያዎች ያሉ፥ የትግራዩ ጦርነት በመሸሽ ሱዳን የገቡ ዜጎች፥ በሱዳን የተቀሰቀሰው ጦርነት አስጊ ሁኔታ ላይ እንደጣላቸው፣ እርዳታ ለጋሾች ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት እንዲሁም የሱዳን ዜጎች አካባቢ ለቀው እየወጡ ቢሆንም እነዚህ ስደተኞች ግን የሚደርስላቸው አጥተው አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆናቸው ያነሳሉ። የትግራይ ተፈናቃዮች ስጋት

30 ሺህ ገደማ የትግራዩ ጦርነት ተፈናቃዮች ተጠልለውበት ከሚገኝ ተነድባ የስደተኞች መጠልያ ያነጋገርናቸው እና ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ራውያን አካባቢ ከልጆቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት እናት ወይዘሮ ጊቱ አለፈ፥ ከሕዳር 2013 ዓመተምህረት ወዲህ በሱዳኑ መጠልያ ኑሮአቸው እንዳደረጉ ይገልፃሉ። ጦርነት ሽሽት የገቡባት ሱዳን ወደ እርስ በርስ ግጭት ማምራትዋ ተከትሎ ግን አሁን ላይ እርሳቸው ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠር ስደተኛ ለአደጋ መጋለጡ ያነሳሉ። ወይዘሮ ጊቱ "ከዚህ በፊት ጦርነቱ ራቅ ባለ አካባቢ ነበር የሚካሄደው እንጂ እኛ ላይ አልደረሰም ነበር። አሁን ግን ወደኛ ቀርቦ፥ እኛጋ የነበሩ የሱዳን ዜጎች ቤተሰቦቻቸው ይዘው ንብረታቸው ስብስባው እየሸሹ ነው። ሱቅ የነበራቸው ሱቃቸው ዘግተው፣ ድርጅቶችም መስርያቤታቸው ዘግተው እየወጡ ነው። እኛ ብቻ ነን መሄጃ አጥተን እዚህ ቁጭ ብለን ያለነው። የሚረዳን ማንም የለም" ብለዋል።

የትግራይ ተፈናቃዮች ምስል Million Haileslasse/DW

ሌላው ከሱዳኑ ተነድባ የስደተኞች መጠልያ ያነጋገርናቸው ከጦርነቱ መቀስቀስ በኃላ በሕዳር ወር 2013 ዓመተምህረት ከአምስት የቤተሰባቸው አባላት ጋር ድንበር ተሻግረው የተሰደዱት አቶ አስማረ አዳል በበኩላቸው የሱዳኑ የእርስ በርስ ግጭት እየተካረረ ባለበት በዚህ ወቅት እርሳቸው መሰል ስደተኛ በማህል አደጋ ላይ መውደቁ ያስረዳሉ። የትግራይ ጦርነት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸዉ መመለስ ጀመሩ

የሌሎች ሀገራት ዜጎች የሱዳኑ ግጭት ከተቀሰቀሰበት ግዜ አንስቶ በመንግስታቶቻቸው በኩል ሀገሪቱ ለቀው እንዲወጡ፣ ወደ ተሻለ ቦታ እንዲዘዋወሩ እየተደረጉ ያለበት ሁኔታ ቢኖርም የኢትዮጵያ መንግስት ግን ለእነዚህ በትግራዩ ጦርነት ወቅት የተሰደዱ ዜጎች ያደረገው ነገር እንደሌለ አቶ አስማረ ጨምረው ይገልፃሉ። የትግራይ ጦርነት ተፈናቃዮች መንግሥት ወደ ቀያቸዉ እንዲመልሳቸዉ ጠየቁ

አነዚህ በሱዳን ተነድባ እና ዑምራኩባ ያሉ በትግራዩ ጦርነት ምክንያት ወደ ሱዳን የተሰደዱ በአጠቃላይ 60 ገደማ የሚገመቱ ስደተኞች የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት፣ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም ዓለምአቀፍ ተቋማትመፍትሔ እንዲያበጁላቸው ይጠይቃሉ። በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። በእነዚህ በሱዳን ያሉ የትግራይ ጦርነቱ ሸሽተው የተሰደዱ ዜጎች ጉዳይ ትላንት በማሕበራዊ የትስስር ገፃቸው የፃፉት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ ግጭቱ መንሰራፋቱ እና ወደስደተኛ መጠልያ ካምፖች መጠጋቱ አሳሳቢ መሆኑ በመግለፅ፥ በዘላቂነት ግጭቱ እንዲቆም ዓለምአቀፍ ማሕበረሰብ ትኩረት እንዲሰጥ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ደግሞ የስደተኞቹ መከራ እንዲያበቃ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚልዮን ኃይለስላሴ
ኂሩት መለሰ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW