1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«በትግራይ መፈንቅለ መንግስት የለም፥ ሕግ እና ስርዓት ማስከበር እንጂ » አቶ አማኑኤል አሰፋ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ዓርብ፣ መጋቢት 5 2017

በትግራይ እየተደረገ ያለ መፈንቅለ መንግስት የለም፥ ሕግ እና ስርዓት ማስከበር እንጂ ሲሉ የህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ አማኑኤል አሰፋ ተናገሩ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት መቀየር ጨምሮ ሌሎች የፕሪቶስያ ውል ያልተፈፀሙ ይዘቶች ለመከወን ከፌደራል መንግስቱ ጋር ንግግሮች ይቀጥላሉ ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል።

አቶ አማኑኤል አሰፋ እና ዶ/ር ፍስሃ ሃብተፂዮን
አቶ አማኑኤል አሰፋ እና ዶ/ር ፍስሃ ሃብተፂዮን ምስል፦ Million Haileselassie Brhane/DW

«በትግራይ መፈንቅለ መንግስት የለም፥ ሕግ እና ስርዓት ማስከበር እንጂ » አቶ አማኑኤል አሰፋ

This browser does not support the audio element.

በትግራይ እየተደረገ ያለ መፈንቅለ መንግስት የለም፥ ሕግ እና ስርዓት ማስከበር እንጂ ሲሉ የህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ አማኑኤል አሰፋ ተናገሩ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ለመቀየር ጨምሮ ሌሎች የፕሪቶስያ ውል ያልተፈፀሙ ይዘቶች ለመከወን ከፌደራል መንግስቱ ጋር ንግግሮች ይቀጥላሉ ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል።

በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ትላንት ማምሻውን ለመገናኛ ብዙሐን ማብራርያ የሰጠው በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ፥ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎችና ከተሞች በምክርቤቶች የተሾሙ ባለስልጣናት የተመደቡበት ስልጣን የማስረክብ፣ "ሕግ የማስከበር" የተባለ ተግባር እየተከወነ መሆኑ አስታውቋል። ማብራሪያ የሰጡት የህወሓት ቡድኑ ከፍተኛ አመራር አቶ አማኑኤል አሰፋ እንደሚሉት በአብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢዎች በአካባቢ ምክርቤቶች የተሾሙ ባለስልጣናት በስራቸው ላይ ያሉ ቢሆንም በመቐለ ጨምሮ በዓዲግራት፣ ዓዲጉደም፣ ሀገረሰላም እና ሌሎች አካባቢዎች ከስርዓት ውጪ ከሀላፊነት ታግደው አልያም በሌሎች ባለስልጣናት ተተክተው የነበሩትን የማስተካከል ስራዎች መከናወናቸውን አመልክተዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ አማኑኤል ይህ በተወሰኑ አካባቢዎች የተደረገ፣ ግዚያዊ አስተዳደሩ ከማፍረስ ጋር የማይገናኝ እንዲሁም "ሕግ የማስከበር" እርምጃ ነው ብለውታል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፌድራል መንግሥት “አስፈላጊ ድጋፍ ማድረግ አለበት” አለ

አቶ አማኑኤል "የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ይሁን ግዚያዊ አስተዳደሩ ለማፍረስ አልያም መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ያለመ አካሄድ፣ ተልእኮ ይሁን ፍላጎት የለም። ስለዚህ አካሄዱ ሕገመንግስታዊ ስርዓት የማክበር፣ ሰላምና ፀጥታ የማረጋገጥ፣ የሕግ የበላይነት የማስከበር ጉዳይ ነው" ብለዋል።

ሰሞኑን በመቐለ፣ ዓዲግራት፣ ዓዲጉደም ጨምሮ ሌሎች አካባቢዎች በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የተሾሙ ባለስልጣናት የመቀየር፣ የአስተዳደር ጽ/ቤቶች በታጣቂዎች ድጋፍ ሰብሮ በመግባት፥ ሐላፊነት ለደብረፅዮኑ የህወሓት ቡድን አመራሮች የማስረከብ እንዲሁም ሌሎች ሕገወጥ እንቅስቃሴዎች እየተከወኑ ነው በማለት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ሲገልፅ የነበረ ሲሆን፥ ይህም 'መፈንቅለ መንግስት' ነው ማለቱም ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪ የህወሓቱ ከፍተኛ አመራር አቶ አማኑኤል አሰፋ በሰጡት ማብራሪያ 'ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚያገናኘን የፕሪቶርያ ውል አለ፣ በውሉ መሰረት ተግባብተን ያልጨረስናቸው አጀንዳዎች አሉ' ያሉ ሲሆን፥ የግዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት ለመቀየርን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮች ለመፈፀም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግንኙነታችን ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል። 

የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናትምስል፦ Million Haileslasse/DW

አቶ አማኑኤል "ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት የሚደረግ ግንኙነት ዛሬም ነገም ይቀጥላል። ስለዚህ መቼ ነው [ወደ አዲስአበባ] የምትሄዱት የሚለው የቀጠሮ ጉዳይ ነው። ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመሆን ነው ግዚያዊ አስተዳደሩን ያቋቋምነው። በተለይም የፕሬዝደንት ቦታ የሚመለከት ደግሞ ሁለታችን የተስማማንበት ነው የሚሆነው። ሁለታችን ያልተስማማንበት እንደማይሆን ከዚህ በፊትም ተረጋግጦ የቆየ ነው። ስለዚህ በግዚያዊ አስተዳደሩ የሚደረግ ማስተካከያዎች ይሁን የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መፈፀም የሚያስችለን ግንኙነት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ይቀጥላል" ሲሉ አክለዋል። የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በሦስት ጀነራሎች ላይ የተላለፈውን እግድ ተቃወመ

ከዚህ በተጨማሪ፥ ህወሓት እንደሚባለው ከኤርትራ መንግስት ጋር ፀረ ኢትዮጵያ መንግስት የሆነ ግንኙነት የለውም ሲሉም አቶ አማኑኤል ጨምረው ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር በክልሉ በፀጥታ ሐይሎች ስም እየተንቀሳቀሱ ያሉት አካላት፥ የአንድ ኋላቀር እና ወንጀለኛ ቡድን ተላላኪ እንጂ የትግራይ ህዝብ እና ግዚያዊ አስተዳደር የማይወክሉ መሆናቸው በመገንዘብ "አስፈላጊ ድጋፍ ማድረግ አለበት" የሚል መልዕክት ለፌደራል መንግስቱ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW