1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ በየሳምንቱ 17 ሺህ ሰዎች በወባ እየተያዙ ነው

ሰኞ፣ ኅዳር 9 2017

በትግራይ ባለፉት 3 ወራት በወባ በሽታ ምክንያት 13 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። የትግራይ ጤና ቢሮ በተለይም ወባን ለመካለከል እና ለመቆጣጠር ከፌደራል መንግስቱ የአቅርቦቶች ድጋፍ እንደሚሻ የሚገልፅ ሲሆን እስካሁን ግን የሚጠበቀው እንዳልተገኘ የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ አረጋይ ገብረመድህን ይናገራሉ።

Äthiopien Gesundheitsstation in Tigray
ምስል Million Hailesilassie/DW

በትግራይ በየሳምንቱ 17 ሺህ ሰዎች በወባ እየተያዙ ነው

This browser does not support the audio element.

በትግራይ የጤና ስርዓቱን መፍረስ ተከትሎ በርካታ በሽታዎች እየተሰራጩ እና የሕብረተሰብ የጤና ስጋት እንደሆኑ ይገለፃል። የትግራይ ጤና ቢሮ እንዳለው፥ በክልሉ በወረርሽኝ መልክ ከተከሰተ የሰነበተው የወባ በሽታ አሁን በከፍተኛ መጠን እየተሰራጨ እና 66 የክልሉ ወረዳዎችን ማዳረሱን አመልክቷል። እንደ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ መረጃ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በየሳምንቱ 17 ሺህ ሰዎች በትግራይ በወባ በሽታ መያዛቸው ተገልጿል። የመድኃኒቶች አቅርቦት አለመኖርና የወባ መከላከያ ግብአቶች አለመዳረስ የበሽታውን ስርጭት ሊያባብሰው ይችላል ተብሎ መሰጋቱ ተነግሯል። በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ አረጋይ ገብረመድህን ለዶቼቬለ እንዳሉት፥ ወባ በትግራይ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ እየተሰራጨ ነው።

በትግራይ በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ60 በመቶ መጨመሩ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ

ጦርነቱ ተከትሎ የጤና ስርዓቱ መፍረስ፣ የሕክምና ባለሙያዎች ውሱንነት፣ የወባ መከላከያ ግብአቶች እና መድኃኒቶች አቅርቦት እጦት፣ የአስተዳደር አካላት ትኩረት አለመስጠት የወባ በሽታ በትግራይ ከዚህ ቀደም ተስተውሎ በማያውቅ ደረጃ እንዲሰራጭ እና ወረርሽኑ አሳሳቢ እንዲሆን እንዳደረገው በተጨማሪነት ተገልጿል።

በተለይም በትግራይ ሰሜን ምዕራብ እና ማእከላዊ ዞኖች የወባ በሽታ በስፋት መሰራጨት መቀጠሉን መረጃዎች ያመለክታሉ። አብዛኛው በወባ የተያዙ ታካሚዎች ምዕድን በማውጣት ስራ የተሰማሩና በረግረጋማ አካባቢዎች የሚኖሩ መሆናቸው የጤና ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

የወባ አስተላላፊ ትንኝ ምስል James Gathany/AP/picture alliance

በአማራ ክልል ከ600 ሺ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸው ተገለጸ

እስካሁን ባሉ መረጃዎች በትግራይ ባለፉት 3 ወራት በወባ በሽታ ምክንያት 13 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። የትግራይ ጤና ቢሮ በተለይም ወባን ለመካለከል እና ለመቆጣጠር ከፌደራል መንግስቱ የአቅርቦቶች ድጋፍ እንደሚሻ የሚገልፅ ሲሆን እስካሁን ግን የሚጠበቀው እንዳልተገኘ የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ አረጋይ ገብረመድህን ይናገራሉ።

 

የበረታው የወባ በሽታ በደቡብ ኢትዮጵያ

በጦርነቱ ምክንያት 80 ከመቶ በሚሆኑ የጤና ተቋማት ላይ በተለያየ ደረጃ የሚገልፅ ውድመት መድረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቆ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ስራ ላይ ያሉ የትግራይ የጤና ተቋማትም በሰው ኃይል ፍልሰት እየተፈተኑ መሆኑ ይገለፃል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ኂሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW