1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በትግራይ ትጥቅ መፍታት እና የወቅቱ የደህንነት ስጋት

ሰኞ፣ መጋቢት 8 2017

በትግራይ ተቋርጦ የነበረው የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ስራ ዳግም ለማስቀጠል መግባባት መደረሱ ተገለፀ። የትግራይ ሐይሎች አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ ሂደቱ ተቋርጦ የነበረው በነበረ ሊፈታ የሚጠበቅ የትጥቅ መጠን አለመግባባት ነው ብለዋል።

Äthiopien General Tadesse Werede TDF
ምስል፦ Million Haileselassie/DW

በትግራይ ትጥቅ መፍታት እና መልሶ ማቋቋም ከምን ደረሰ?

This browser does not support the audio element.

በትግራይ ተቋርጦ የነበረው የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ስራ ዳግም ለማስቀጠል መግባባት መደረሱ ተገለፀ። የትግራይ ሐይሎች አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ ሂደቱ ተቋርጦ የነበረው በነበረ ሊፈታ የሚጠበቅ የትጥቅ መጠን አለመግባባት ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን በትግራይ 8 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች የተሃድሶ ስልጠና ሰጥቶ ወደ መደበኛ ሕይወት እንዲመለሱ ማድረጉን ገልጾ ነበረ።

አንድ ግዜ እየጦዘ ሌላ ግዜ እየረገበ ለወራት እየቀጠለ የነበረው የህወሓት የውስጥ ክፍፍል፥ አሁን ላይ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሶ፥ ግጭቶች የሚፈጠሩበት በዚሁ ግጭቶች ምክንያት ደግሞ ዜጎች የሚጎዱበት ሁኔታ መታየት ጀምሯል። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በክልሉ መፈንቅለ መንግስት እየካሄደ ነው በማለት የህወሓት አንድ ቡድን እና የትግራይ ሐይሎች አካል የሆኑ ታጣቂዎች መወንጀሉ ተከትሎ ደግሞ፥ ምናልባትም ከፈደራል መንግስት ጋር ዳግም ግጭት እንዳይነሳ በበርካቶች ስጋት ተፈጥሮ ሰንብቷል።

«በትግራይ መፈንቅለ መንግስት የለም፥ ሕግ እና ስርዓት ማስከበር እንጂ » አቶ አማኑኤል አሰፋ

በሌላ በኩል ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ለመገናኛ ብዙሐን መግለጫ ሰጥተው የነበሩት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት እና የትግራይ ሐይሎች ዋና አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ በትግራይ ውስጥ ይሁን ከፌደራል መንግስት ጋር ግጭት አይፈጠርም ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጀነራል ታደሰ ወረደ በመግለጫቸው በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ ከወራት በፊት ተጀምሮ የነበረ ስራ አስመልክተው የተናገሩት ጀነራሉ በተፈጠሩ አለመግባባቶች ተቋርጦ መቆየቱ ያነሱ ሲሆን፥ ዋናው የአለመግባባቱ መነሻም ደግሞ የፌደራል መንግስት ከተጠየቀው የሚፈታ የትጥቅ መጠን ጋር የተገናኘ መሆኑ ገልፀዋል።

ትግራይ ሐይሎች አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ ሂደቱ ተቋርጦ የነበረው በነበረ ሊፈታ የሚጠበቅ የትጥቅ መጠን አለመግባባት ነው ብለዋልምስል፦ Million Hailessilasie/DW

በትግራይ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ

ጀነራል ታደሰ "የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ ማስፈታት ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለስ ተግባር ተቋርጦ ነበረ። የቆመበት ምክንያት ትጥቅ በሚመለከት የነበረ አለመግባባት ነው። እንዲወርድ እየተጠየቅነው የነበረ የትጥቅ መጠን ላይ የነበረ አለመግባባት ነበር። የሚጠየቀው የትጥቅ ቁጥር ከመጠን በላይ ነበር" ብለዋል።

ይህ አለመግባባት ለመፍታት ጀነራሉ ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር ውይይት ማድረጋቸው እና መግባባት መደረሱም ያነሱ ሲሆን "ማድረግ የሚገባን መግባባት ነበር። አዲስአበባ ሄጄ ከመከላከያ ጋር በትጥቅ ጉዳይ መግባባት አድርገን፣ ምክንያታዊ አድርገን ዓርብ [ያለፈው] ዳግም የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ ማስፈታት እና ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለስ ስራ ሊቀጥል ተብሎ ነበር። አሁን ላይ የተባባልነው ደግሞ ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት እናርግብ የሚል ነው። ይህ የብቻችን ውሳኔ ሳይሆን ከፌደራል መንግስቱ ጋርም መግባባት የደረስንበት ነው።ይህ በአጭር ግዜ ይፈታል። በአጭር ግዜ ደግሞ ወደስራዎቻችን እንገባለን" ሲሉ ጀነራል ታደሰ ወረደ ጨምረው ገልፀዋል።

የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በሦስት ጀነራሎች ላይ የተላለፈውን እግድ ተቃወመ

የሁለት ዓመቱ ጦርነት ባስቆመ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሰረት ተጀምሮ የነበረው የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎች ወደ የተሃድሶ ማእከላት የማስገባት ስራ፥ በተለያዩ ዙሮች 75 ሺህ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት የመመለስ ስራ ለመከወን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን በኩል ታቅዶ የነበረ ቢሆንም 8 ሺህ ገደማ የቀድሞ ታጣቂዎች በሂደቱ ካለፉ በኃላ ስራው መቋረጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW