በትግራይ እየተካሄደ ባለው ውጊያ የተለያዩ ማህበረሰቦች ተወካዮች አስተያየት
ረቡዕ፣ ኅዳር 9 2013ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና ትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው "ህወሓት" መካከል ሲስተዋል የነበረው ሽኩቻ ከጥቅምት 24ቱ የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ጥቃት ወዲህ ወደ ውጊያ ተሸጋግሮ በርካቶችንም የተለያዩ አስተያየቶችን እያሰጠ ነው፡፡
በአንድ በኩል "ለድርድር አይመሽም" በሚል አሁንም ሃሳቦችን ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ማምጣት ተገቢ ነው የሚል ሃሳብ ሲነሳ በሌላ በኩል ደግሞ የፌዴራል መንግስት "የህግ የበላይነት እና የሃገር አንድነትን የማስከበር ኦፕሬሽን ነው" ያለውን ውጊያ አስገዳጅ ይሉታል፡፡
አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ፖለቲከኞችና የተለያዩ የማህበረሰብ ተወካዮች ጦርነቱ እስካሁንም ያደረሰው ሰብዓዊ ቀውስ ከመኖሩም ባለፈ፤ "ኦፕሬሽን" ከተባለው ውጊያ በኋላም ሊከተል የሚችለውን ስጋትና ተስፋዎችን አስቀምጠዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ