በትግራይ ክልልና በአካባቢዉ ያንዣበበዉ የጦርነት ሥጋት
ዓርብ፣ ጥቅምት 28 2018
ማስታወቂያ
የትግራይ ክልል ታጣቂዎች የክልሉን ድንበር ተሻግረዉ አፋር ክልል፣ ዞን ሁለት ዉስጥ 6 ቀበሌዎችን አጥቅተዋል መባሉ ወትሮም ዉጥረት የተጫጫነዉን አካባቢ ከዳግም ጦርነት እንዳይከተዉ አስግቷል።የአፋር ክልል መስተዳድርባለፈዉ ሮብ (ጥቅምት 26) ባወጣዉ መግለጫ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጭምር አደረሱት ያለዉን ጥቃት አጥብቆ አዉግዟል።የትግራይ ክልል ተቃዋሚ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ደግሞ «አጥፎ ጠፊ» ያለዉ የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት፣ ከኤርትራዉ ሻዕቢያ ጋር በመሆን ጦርነት አዉጀዋል ብሏል።
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ግን ተፈፀመ የተባለዉን ጥቃት አስተባብሏል።ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት ደግሞ የኢትዮጵያ የመከላከያ ጦር ትግራይ ዉስጥ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ማከማቻ መጋዘንን በሰዉ አልባ አዉሮፕላን ደብድቧል።ደረሱ የተባሉት ጥቃቶች፣ የቃላት ዉግዘትና አፀፋ ዉግዘቱን በተመለከተ ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሄርን አነጋግሬዋለሁ።
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ