በትግራይ የቦንብ ፍንዳታና የጉዳቱ መጠን
ሰኞ፣ ሚያዝያ 18 2002ማስታወቂያ
በዚህ ፍንድታ 20 ሰዎችም ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአደጋዉ ሁኔታና የጉዳቱ መጠን ምን እንደሚመስል ወደአካባቢዉ ስልክ በመደወል የጉዳት ሰለባዎቹን ቤተሰቦች ያነጋገረዉ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ከድሬደዋ ዘገባ ልኮልናል። በማያያዝም ባለፈዉ ቅዳሜ በሰሜናዊ ትግራይ አካባቢ በተፈፀመዉ የቦምብ ፍንዳታ የኤርትራ መንግስት እጅ እንዳለበት የጠቆሙት የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ፀጋዬ በርሄ ድርጊቱ ምርጫዉን ለማደናቀፍ ነዉ ብለዉታል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የምታቀርበዉ ይህን መሰል ክስ ምን መነሻ ይኖረዋል? ይህና ሌሎች ጥያቄዎችን በማንሳት የምስራቅ አፍሪቃ የፖለተካ ተንታኝ የሆኑትን አቶ ዩሱፍ ያሲንን ያነጋገረዉ መሳይ መኮንን ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሯል፤
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
መሳይ መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ