1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ የጸረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድኃኒት አቅርቦት ችግር

ሐሙስ፣ ኅዳር 22 2015

በትግራይ የሚገኙ የኤች አይ ቪ ኤድስ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች በመድሃኒት እጦት ምክንያት እየተሰቃዩ መሆኑ ገለፁ። ዓለም አቀፉን የኤድስ ቀን አስመልክቶ የትግራይ ጤና ቢሮ በሰጠው መግለጫ በትግራይ ክልል የነበሩ ከ46 ሺህ በላይ የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት ተጠቃሚዎች ለወራት መድሃኒቱ ባለማግኘታቸው አደጋ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

HIV AIDS in Afrika | Kenia Nairobi Infizierter mit Medikament
ምስል Donwilson Odhiambo/ZUMA/picture alliance

የጸረ ኤች አይ ቪ ኤድስ አቅርቦት ችግር በትግራይ ክልል አሳሳቢ ሆኗል

This browser does not support the audio element.

በትግራይ የሚገኙ የኤች አይ ቪ ኤድስ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች በመድሃኒት እጦት ምክንያት እየተሰቃዩ መሆኑ ገለፁ። ዓለም አቀፉን የኤድስ ቀን አስመልክቶ የትግራይ ጤና ቢሮ በሰጠው መግለጫ በትግራይ ክልል የነበሩ ከ46 ሺህ በላይ የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት ተጠቃሚዎች ለወራት መድሃኒቱ ባለማግኘታቸው አደጋ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።  በዚህም  በግብአቶች እጦት ምክንያት በክልሉ የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል።

ወይዘሮ አዝመራ አሸብር በትግራይ ካሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ለዓመታት የፀረ ኤችአይቪ ቫይረስ መከላከያ መድሃኒት ተጠቃሚዎች ከነበሩት መካከል ናቸው። አሁን ላይ ወይዘሮ አዝመራ ጨምሮ በርካታ በትግራይ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ዜጎች ይጠቀሙት የነበረ ፀረ ኤችአይቪ ኤድስ መድሃኒት እያገኙ እንዳልሆነ ይገልፃሉ። ወይዘሮ አዝመራ ቫይረሱ በደማቸው መኖሩ ካረጋገጡ በኃላ ላለፊት 16 ዓመታት ፀረ ቫይረሱ መድሃኒት ሳያቋርጡ መውሰዳቸው ተከትሎ ጤናቸው እየተሻሻለ፣ በሂደት ከቫይረሱ ነፃ የሆኑ ልጆች ወልደው እያሳደጉ እንደቆዩ ነግረውናል። ይሁንና አሁን ጦርነቱ ተከትሎ በተፈጠረ ሁኔታ መደበኛ መድሃኒት የሚገኝበት ዕድል ጠፍቶ፥ ላለፊት ከ30 በላይ ቀናት መድሃኒታቸው አቋርጠው ይገኛሉ። ወይዘሮ አዝመራ "የፀረ ቫይረሱ መድሃኒት የማግኘት ነገር እንደ መርፌ ቀዳዳ የጠበበ ሆኖ ነው ያለው። ላለፊት ወራት የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች እርስ በርሳችን በእጃችን የነበረ እየተካፈልን ነበር ስንጠቀም የነበርነው። አሁን ሁሉ ጨርሷል። በዚህ መድሃኒት ከቫይረሱ ነፃ የወለድኳቸው ልጆች እያሳደግኩኝ ለመኖር ነበር ምኞቴ" የሚሉት ሲሆን "ይሁንና አሁን መድሃኒት የለም። ሕይወት ጨለማ ነው የሆነብኝ፣ አይደለም ሰላሳ ቀናት አንድ ቀን እንኳን መቋረጥ የሌለበት መድሃኒት አቋርጬ ነው ያለሁት" ሲሉ አክለዋል።ቀጣዩ ክትባት የኤች አይ ቪ ኤድስ ይሆን?

ተስፋ ሕይወት የተባለ በትግራይ ያሉ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሴቶች ሕብረት እንደሚገልፀው በመድሃኒቱ መቋረጥ ምክንያት በርካቶች እየሞቱ፣ ለከፍተኛ የጤና ችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ጤና ቢሮ ዓለምአቀፉ የኤድስ ቀን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በመድሃኒቱ እንዲሁም ሌሎች መከላከያ እና ማከሚያ ግብአቶች እጥረት ምክንያት በትግራይ የኤችአይቪኤድስ ስርጭት እየጨመረ እንዳለ አስታውቋል።አሳሳቢው የኤድስ አስተላላፊ ተኀዋሲ ስርጭት

እንደ የትግራይ ጤና ቢሮ መረጃ በትግራይ ከ46 ሺህ በላይ ፀረ ቫይረሱ መድሃኒት ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን፣ በመድሃኒት እጦቱ ምክንያት እነዚህ ዜጎች አሁን አደጋ ላይ ናቸው። ከመድሃኒት እጦቱ በተጨማሪ ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ይደረግ የነበረ ክትትልም በግብአት እጥረት ተስተጓጉሎ እንዳለ የጤና ባለሙያዎች ገልፀውልናል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW