1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በኑዌር ዞን ላረ ወረዳ 7ሺህ የሚደርሰ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው መመለሳቸው

ዓርብ፣ ጥቅምት 7 2018

በጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን ላረ ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ተፈናቅለው ከነበሩ መካከል ሰባት ሺህ የሚደርሱ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸው የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።

ጋምቤላ ባሮ ወንዝ
በነሐሴ ወር የወረደው ዝናብ ለባሮ ወንዝም ሙላት አስተዋጽኦ አድርጎ ነበር። ፎቶ ከማኅደርምስል፦ privat

ጎርፍ ያፈናቀላቸው ገሚሱ መመለሳቸው

This browser does not support the audio element.

 

በምዕራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን ላረ ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ተፈናቅለው ከነበሩ መካከል ሰባት ሺህ የሚደርሱ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸው የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ። በነሐሴ ወር የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ከወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ዜጎች በደረቃማ ቦታዎች ላይ ሰፍረው መቆየታቸውን የወረዳው አደጋ ስጋት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት የአደጋ ምላሽ ሀላፊ አቶ ታንኩይ ኒድ ገልጸዋ። የተመለሱ ዜጎችም በርካታ ሰብል ቁም እንስሳት እንደተጎዳባቸው በመግለጽ ከተፈናቀሉ ጊዜ አነስቶ ሰብአዊ ድጋፍ አለማግኘታውን አመልክተዋል። በአኙዋ ዞን ጆር ወረዳ ደግሞ የጎርፍ መጥለቅለቅ መከሰቱን የወረዳው አስተዳደር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያመለከተ ሲሆን በጎርፍ የደረሰ ጉዳት ይኑር አይኑር ግን ያለው ነገር የለም።

በላሬ ወረዳ በነሐሴ ወር 12ሺ100 የሚደርሱ ሰዎች በጎርፍ ተፈናቅለዋል

በጋምቤላ ክልል በክረምት ወራት የባሮ ወንዝና ጊሎ ወንዞች ሙላት በተለያዩ ወቅቶች በወንዝ ዳርቻ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ጉዳት ሲያደርሰ መቆየቱን የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት መረጃ ያመለክታል። በኑዌር ብሔሰብ ዞን የዞኑ ዋና ከተማን ጨምሮ  በላረና ጅካዎ ወረዳ በነሐሴ ወር በጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ሰዎች ተፈናቅለዋል። በዞኑ ላረ ወረዳ ከ12 ሺህ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታው ተፈናቅለው እንደነበር የወረዳው የአደጋ ስጋት አገልግሎት አመልክተዋል።

በወረዳው በቁም እንስሳት እና ሰብል ላይ ጉዳት መድረሱን የተናገሩት የላረ ወረዳ አደጋ ስጋት አገልግሎት ጽ/ቤት አደጋ ምላሽ ሀላፊ አቶ ታንኮይ ኒድ ተፈናቀለው ከነበሩት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ወደ ቀድሞ ቀያቸው መመለሳቸውን አብራርተዋል። በክረምት ወቅት ወረዳው ጅካዎ የተባለ ወንዝ ሙላት እና ከፍተኛ መጠን ባለው ዝናብን ተከትሎ ጎርፍ ጉዳት እንደሚያስከትል የተናገሩት አቶ ታንኮይ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ወደ ደረቃማ ቦታዎች እንዲዛወሩ ተደርጎ እንደነበር አመልክተዋል።

በላሬ ወረዳ በነሐሴ ወር የጣለው ዝናብ ባስከተለው ከፍተኛ መጠን ያለው ጎርፍ የሰብል ማሳ መበላሹቱን የነገሩን ጃክ የተባሉ የአካባቢውነዋሪ በጎርፍ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀድሞ ቤታቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ለሁለተ ወራት ያህል በመጠለያ ጣቢያ ለነበሩ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ እስካሁን እንዳልተሰጣቸው በመግለጽ በስፍራው በርካቶች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን አመልክተዋል። በጎርፍ ሳቢያ በሰብል እና በቁም እንስሳት ላይ ጉዳት ደርሶ እንደነበር ገልጸው ከተፈናቀሉት ከሦስት ቀበሌዎች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች መመለሳቸውን ተናግረዋል።

በክረምቱ ምዕራብ ኢትዮጵያ ላይ የወረደው ዝናብ ጋምቤላ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች በጎርፍ እንዲጥለቀለቁና ብዙዎችም እንዲቀናፈሉ አድርጓል።ፎቶ ከማኅደር ምስል፦ Itang woreda administration

‹‹ለሁለት ወራት ሰብአዊ ድጋፍ አላገኘኝም›› የተፈናቀሉ ዜጎች

በጎርፍ ምክንያት ተፈናቅለው ለሁለት ወር ያህል በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ መቆየታቸውን የተናገሩት ጋሉዋክ የተባሉ ሌላው የአካባቢው ነዋሪ «ጉሉንኩም» ወደተባለው መኖሪያ አካባቢያቸው መመለሳቸውን አመልክተዋል። በጎርፉ ብዙ ንብረታቸው መውደሙን የተናገሩት አቶ ጋሉዋክ ሰብአዊ ድጋፍ እስካሁን ባለማግኘታቸው ለችግር መጋለጣቸውን ጠቁመዋል።

በክረምት ወራት በተለይም በሐምሌ እና ነሐሰ ወራት ከባድ መጠንያለው ዝናብ ጎርፍና የመሬት መንሸራተቶችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሜትሮሊዎጂ ኢንስቲትውት ሲያሳስብ ቆይቷል። በነሐሴ ወር በኑዌር ብሔረሰብ ዞን ዋና ከተማ «ኝንኛንግ» የተባለ ከተማ በተሰመሳሳይ የጎርፍ መጥለቅለቅ አጋጥሞት እንደነበር ተዘግቧል። የተፈናቀሉ ዜጎችን ሰብአዊ ድጋፍ ጥያቄን በተመለከተ ከክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር አገልግሎት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት ስልክ ባለማንሳታቸው አልተሳካም።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW