በኒሻንጉል ክልል ታጣቂዎች ሰዉ ገደሉ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 29 2013ማስታወቂያ
በበኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንነታቸዉ በዉል ያልታወቀ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት በትንሹ 10 ሠላማዊ ሰዎች ገደሉ።ጥቃቱ የደረሰበት የድባጤ ወረዳ ቂዶ ቀበሌ ነዋሪዎች እንዳሉት ታጣቂዎቹ ባለፈዉ ዕሁድ ከ4 ሰዓት ጀምሮ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉት ሰዎች አብዛኞቹ በዕለታዊ ሥራቸዉ ላይ የነበሩ ነበሩ።በጥቃቱ ተደናግጠዉ የጠፉ ወይም በታጣቂዎቹ የታግቱ ሰዎች ያሉበት አለመታወቁንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።የመተከል ዞን የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ወይም ኮማንድ ፖስት በዳንጉር ወረዳ የሚንቀሳቀሱ «ፀረ-ሠላም» ኃይላት ባላቸዉ ባላቸዉን 23 ሰዎች ላይ ዕርምጃ መዉሰዱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ አስታዉቋል።የዕርምጃዉ ምንነት አልተብራራም።
ነጋሳ ደሳለኝ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ