1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

በኒውዮርክ የግራ ክንፍ ፖለቲከኛ በከንቲባነት ማሸነፍ አነጋጋሪ ሁኗል

ረቡዕ፣ ጥቅምት 26 2018

በዩናይትድ ስቴትስ የኒውዮርክ ምርጫ የግራ ክንፉ ፖለቲከኛ ዞኽራን ማምዳኒስ የከተማዪቱ ከንቲባነትን ማሸነፋቸው አነጋጋሪ ሁኗል ። የአሜሪካ ዴሞክራቶች የግራ ክንፍ ዴሞክራቱ ስለማሸነፋቸው ብዙም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል ። የአውሮጳ የግራ ክንፍ ፖለቲከኞች ግን ከወዲሁ ደስታቸውን እየገለጡ ነው ።

USA New York | Zohran Mamdani Bürgermeisterwahl
ምስል፦ Shannon Stapleton/REUTERS

በኒውዮርክ ግራ ፖለቲከኛ እንዴት ሊያሸንፉ ቻሉ?

This browser does not support the audio element.

በዩናይትድ ስቴትስ የኒውዮርክ ምርጫ የግራ ክንፉ ፖለቲከኛ ዞኽራን ማምዳኒስ የከተማዪቱ ከንቲባነትን ማሸነፋቸው አነጋጋሪ ሁኗል ። የአሜሪካ ዴሞክራቶች የግራ ክንፍ ዴሞክራቱ ስለማሸነፋቸው ብዙም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል ።

የአውሮጳ የግራ ክንፍ ፖለቲከኞች ግን ከወዲሁ ደስታቸውን እየገለጡ ነው ። ዞኽራን ማምዳኒ በኒውዮርክ ምርጫ በከንቲባነት ሲያሸንፉም የመጀመሪያው ሙስሊም ናቸው ። ልክ እንደ ለንደን ከንቲባ ሣዲቅ ካን ሁሉ ዞኽራን ማምዳኒ በበዩናይትድ ስቴትስ  ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ  የቃላት ጥቃት ደርሶባቸው እንደነበር በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች ተዘግቧል ።

በመላው  ዩናይትድ ስቴትስ በተከናወነው የመካከለኛው የሥልጣን ዘመን ምርጫ (mid term election) በተለያዩ ግዛቶች ተከናውኗል ። በብዙ ቦታዎች ዴሞክራቶች ማሸነፋቸው ተገልጧል ።  ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ የዋሽንግተን ወኪላችን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬው ነበር ። አበበ፦ የምርጫ ውጤቱ  በትራምፕ አስተዳደር  ላይ ያለው አንደምታ ምንነትን በማብራራት ይጀምራል ።

ለመሆኑ እንዲህ አነጋጋሪ የሆኑት ሰውዬ ማን ናቸው? እንዴትስ የዴሞክራቶቹ ከተማ በሆነችው ኒውዮርክ ሊያሸንፉ ቻሉ?

ዞኽራን ማምዳኒስ በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አይወደዱም ። እንደውም ፕሬዚደንቱ ኒውዮርክ ከተማ ላይ ጫና እንደሚያሳድሩ ዝተዋል ። በአንጻሩ ደግሞ የአውሮጳ የግራ ክንፍ ፖለቲከኞች ከወዲሁ ደስታቸውን እየገለጡ ነው ። ይኼ ምንን ያሳያል?

ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከድምፅ ማገናኛው ማድመጥ ይቻላል ።

አበበ ፈለቀ/ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW